የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተለያዩ ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጐማዎች፣ ባትሪዎች፣ ያገለገሉ የከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ፣ ያገለገሉ ኤጋና ቆርቆሮዎች፣ ያገለገሉ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ያገለገሉ ዩፒኤስ እና ሌሎች ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎች
ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተለያዩ ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጐማዎች፣ ባትሪዎች፣ ያገለገሉ የከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ፣ ያገለገሉ ኤጋና ቆርቆሮዎች፣ ያገለገሉ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ያገለገሉ ዩፒኤስ እና ሌሎች ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ተጫራች:-
- ከላይ የተጠቀሱትን ንብረቶች ያሉበትን ሁኔታ በድርጅቱ በመገኘት ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ጨረታ መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማየት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ/ በመክፈል ከማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መውሰድ ይችላል፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎችን የያዘ የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- ጨረታው ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በአጭር የስልክ ቁጥር 8868 ወይም በ0114-16-39-78/68 ይደውሉ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
