Tender Detail

Tender Details

  • Company Riders Trading and Manufacturing S.C (ራይደርስ ትሬዲንግና ማኑፋክቸሪንግ አ.ማ)
  • Address አዳማ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 251944334484
  • Website
  • Deadline03 Dec 2024, 9:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cargo Vehicle

ኩባንያችን ራይደርስ ትሬዲንግ እና ማኑፋክቸሪንግ አ.ማ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል።

Riders Trading and Manufacturing S.C (ራይደርስ ትሬዲንግና ማኑፋክቸሪንግ አ.ማ)


የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን ራይደርስ ትሬዲንግ እና ማኑፋክቸሪንግ አ.ማ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል። በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ፡-

  1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር የያዘውን የመወዳደሪያ ሰነድ አዲስ አበባ ሳር ቤት JFK አፓርትመንት ምድር ላይ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የጨረታ ዋጋውን 20% (ሃያ በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ዋጋ በታሸገ ፖስታ በማዘጋጀት ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ መግዛት ይችላሉ።
  4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ15ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ተዘግቶ 3፡30 የአክሲዮን ማህበሩ ንብረት በሆነው አዳማ ራይደርስ ኤልሴ ቴክስታይል ኢንዱስትሪ በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  5. የጨረታው አሸናፊ በደብዳቤ ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ከፍሎ ተሽከርካሪውን ማንሳት አለበት። በተጠቀሰው ቀን ውስጥ ካላነሱ የጨረታው አሸናፊ ያስያዘው የጨረታ ማስረከቢያ ገንዘብ ለአክሲዮን ማህበሩ ገቢ ሆኖ ንብረቱ ለ2ኛ አሸናፊ የሚሰጥ ይሆናል።
  6. የተሽከርካሪውን የስም ዝውውርና ህግ የሚጠይቃቸውን ማንኛውም ክፍያዎች (ወጪዎች) አሸናፊ የሚሸፍን ይሆናል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት ዕለት ጀምሮ አዳማ ራይደርስ ኤልሴ ቴክስታይል ኢንዱስትሪ በመገኘት ለጨረታ የቀረቡ ከባድ እና ቀላል የጭነት መኪኖቹን ጠቅላላ ሁኔታ ዘወትር በስራ ሰዓት ቀርበው ማየት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል።
  9. አ/ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ +251944334484/+251922755321

ራይደርስ ትሬዲንግና ማኑፋክቸሪንግ አ.ማ

Save Tender