በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላድንጋይ አጠ/2ኛ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ፤ የህንፃ ቁሳቁሶች አላቂ የፅህፈት መሳሪያ የቤተ ሙከራ ቁሳቁሶች የስፓርት ማቴሪያሎች የፅዳት ቁሳቁሶች በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላድንጋይ አጠ/2ኛ/ደ/ት/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላድንጋይ አጠ/2ኛ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ፤ የህንፃ ቁሳቁሶች አላቂ የፅህፈት መሳሪያ የቤተ ሙከራ ቁሳቁሶች የስፓርት ማቴሪያሎች የፅዳት ቁሳቁሶች በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ተጫራቾች ፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የገዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1ኛ-2ኛ የተጠቀሱትን እና ይጠቅመኛል የሚሉትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቹ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የእቃዎችን አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከት/ቤቱ ከዋና ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር /የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ መሂ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በት/ቤቱ ር/መ/ር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን 4፡30 ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፤
- የጨረታ መዝጊያ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበአል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 5፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ የት/ቤቱ ስ/ቁ፡- 0116250226 መደወል ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፤ አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደብረብርሃን ከተማ 72 ኪ.ሜ ወደ ደሴ መስመር በሚወስደው መንገድ ጣ/በር ዋሻ ወደ ምዕራብ 22 ኪ.ሜ ገባ ብሎ መሆኑን እንገልፃለን።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላድንጋይ አጠ/2ኛ/ደ/ት/ቤት
