የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የተለያዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና አገልግሎት የሚውል አሸዋ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Addis Ababa City Roads Authority (የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አአከመባ/ግብዓት/ቡ-1/012-2/2017
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የተለያዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና አገልግሎት የሚውል አሸዋ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የሚገዛው ዕቃ ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ መለያ ቁጥር |
ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ |
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በብር |
|
1 |
አዋሽ |
ሜ.ኩ |
14,151 |
አአከመባ/ ግብዓት/ ቡ-1/012-2/2017 |
60 ቀን |
ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 |
ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 |
500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር / |
ስለዚህ ፡-
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይንም ድረ ገፅ መመዝገብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ተጫራቾች በህግ አግባብነት ካለው አካል የተሰጠ አሸዋ ለገበያ ማቅረብ የሚያስችል የማምረቻ ቦታ እና የባለቤትነት ፍቃድ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ/ ውክልና ማስረጃ የተረጋገጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ውክልና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከባለሥልጣኑ መ/ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 135 መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የአሸዋ ምርት በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው መሠረት በሁለት ከረጢት ከአንድ አይነት የአሸዋ ማምረቻ ቦታ የተወሰደ እያንዳንዱ 25 ኪሎ ግራም በድምሩ 50 ኪ.ግ የአሸዋ ናሙና በባለስልጣን መ/ቤቱ መካኒሳ ዕቃ ግ/ቤት ጨረታውን አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ ብቻ በባለሥልጣኑ መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 በተዘጋጀው ሳጥን ውስት ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ይከፈታል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር ፡- 011-3-72-28-15/0113-71-41-03
አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን
