በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬ ከተማ አስተዳደር በኤፌሶን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለከተማው የውሃ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የቢሮ ዕቃዎችና የፅህፈት መሳሪያ ፣ የሰራተኛች ጥቅማጥቅም፤ የፅዳት መገልገያ ዕቃዎች ፤ ደንብ ልብስ ብትን ጨርቅና የተዘጋጁ ልብሶች እና የቧንቧ መገጣጠሚያ ዕቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬ ከተማ አስተዳደር በኤፌሶን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬ ከተማ አስተዳደር በኤፌሶን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለከተማው የውሃ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የቢሮ ዕቃዎችና የፅህፈት መሳሪያ ፣ የሰራተኛች ጥቅማጥቅም፤ የፅዳት መገልገያ ዕቃዎች ፤ ደንብ ልብስ ብትን ጨርቅና የተዘጋጁ ልብሶች እና የቧንቧ መገጣጠሚያ ዕቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ መወዳደር የምትፈልጉ።
- በዘርፉ የተመዘገበና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የግዥ መጠኑ ብር 200000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)
- ከዚህ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት መረጃ ኮፒ ከፖስታው ጋር ማቅረብ የሚችል ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1% እና ከዚያ በላይ ማሲያዝ እንደሚጠበቅባቸውና ይኸውም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤታችን ገቢ ደረሠኝ በመቁረጥ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሠነዱ ጋር አብራችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾ በጨረታ መክፈቻ ወቅት እንዲገኙ አይገደዱም። ነገር ግን በጨረታ መገኘት አለብን ብለው ካሰቡ መገኘት ያለበት አካል የተጫረተው ባለቤት/ ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው አካል ኦርጂናል የውክልና ማስረጃውን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሱት ሎቶች ሠነድ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በያንዳንዱ ሎት በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከኤፌሶን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወያያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የወሰዱት የተጫራቾች መመሪያ ወይም የጨረታ ዶክሜንት/ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግና በመፈረም ሳይቀንሱ መመለስ ይጠበቅባቸዋል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ውድድሩ የሚካሄደው በየሎቱ በጥቅል ድምር ሆኖ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ አሸናፊ ስለሚሆን እያንዳንዱ የዋጋ ዝርዝር መሞላት አለበት:: ይህ ካልሆነ ግን ከውድድር ውጪ ይሆናሉ።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ እንደተገለጸለት ባሉት ቀናት ውስጥ ውለታ በመግባት እቃዎቹን ኤፌሶን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገሎት ጽ/ቤት ድረስ ማስረከብ ይኖርበታል።
- ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በስልከ ቁጥር 0336610092 መደወል ይችላሉ።
በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬ ከተማ አስተዳደር የኤፌሶን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
