Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ኦፕቶሜትሪ ባለሙያዎች ማኅበር
  • Address አራት ኪሎ፣ ቱሪስት ሆቴል ጀርባ፣ ተስኒም ሕንጻ ሁለተኛ ፎቅ ፤ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0910038040
  • Website
  • Deadline27 Nov 2024, 4:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የኢትዮጵያ አፕቶሜትሪ ባለሙያዎች ማኅበር በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አዋጅ 1113/2011 በኤጀንሲው ቁጥር 2913 የተመዘገበ የሙያ ማኅበር ሲሆን ከህዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ያለውን የማኅበሩን የሂሳብ ሥራ በውጪ አዲተር ማስመርመር ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ድርጅቶችን በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ ኦፕቶሜትሪ ባለሙያዎች ማኅበር


አስቸኳይ  ግልፅ  የጨረታ  ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አፕቶሜትሪ ባለሙያዎች ማኅበር በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አዋጅ 1113/2011 በኤጀንሲው ቁጥር 2913 የተመዘገበ የሙያ ማኅበር ሲሆን ከህዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ያለውን የማኅበሩን የሂሳብ ሥራ በውጪ አዲተር ማስመርመር ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ድርጅቶችን በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል።

  1. የሰርቲፋይድ ቻርተርድ አካውንታንት የሆኑና አዲት የማድረግ ሕጋዊ የሙያ ፈቃድ እንዳላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች በዘርፉ ለ2017 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም ጨረታው እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ ሊያገለግል የሚችል የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ ክሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት (የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት) እና 5000.00 ብር (አምስት ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡ ሆኖ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ቫትን ያካተተ ፋይናንሽያልና ቴክኒካል ፕሮፖዛል በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለማኅበራችን ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድና መመሪያ አንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከ2፡30-10፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል አራት ኪሎ፣ ቱሪስት ሆቴል ጀርባ፣ ተስኒም ሕንጻ ሁለተኛ ፎቅ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኦፕቶሜትሪ ባለሙያዎች ማኅበር ቢሮ መግዛት የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች ሥራውን ሠርተው የሚጨርሱበትን ቀን በመጥቀስ ማስገባት የሚችሉ።
  5. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0910038040 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻችን ፡- አራት ኪሎ፣ ቱሪስት ሆቴል ጀርባ፣ ተስኒም ሕንጻ ሁለተኛ ፎቅ፣

 

የኢትዮጵያ  ኦፕቶሜትሪ  ባለሙያዎች  ማኅበር

Save Tender