በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጤና ቢሮ ከመደበኛ የተገኘ የበጀት ድጋፍ በክልሉ ስር ለሚገኙ ጤና ተቋማት እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የህክምና መሳሪያ በግልፅ በጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾኛ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
Amhara Health Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጤና ቢሮ ከመደበኛ የተገኘ የበጀት ድጋፍ በክልሉ ስር ለሚገኙ ጤና ተቋማት እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የህክምና መሳሪያ በግልፅ በጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾኛ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው:
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ሰርተፍኬት/ የሚያቀርብ፡፡
- ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የሚገዛው ዕቃ ከጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቫት ሰርቲፊኬት ኮፒ ማስያዝ አለበት።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ ብር 500,000.00 አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዝ፤
- ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሃሳቡን በታሸገ ፖስታ በጤና ጥበቃ ቢሮ የግዥ ፋይ ንብ/አስ ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾቸ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል/በቢሮ ፋይናንስ ህንፃ በ16ኛው ቀን 2017 ዓ.ም በ 8፡30 ሰዓት ታሽጎ 9፡00 ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸገና የሚከፈት ይሆናል።
- ቢሮው የግዥን መጠን እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት እስከ 11፡30 እና በአስራ ስድስተኛው ቀን እስከ 8፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 1000 / አንድ ሺህ/ ብር በመክፈል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 213 ድረስ በአካል ቀርቦ መግዛት ይችላል።
- የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጭ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ መጋዘን ድረስ ማቅረብ አለበት።
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ ጨረታውን ላወጣ መስሪያ ቤት ለአብከመ ጤና ጥበቃ ቢሮ ፋይናንስ ህንፃ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582221127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል።
የአብክመ ጤና ቢሮ /ባህር ዳር/
