የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ህዳሴ ቦሌ ሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ ህብረት ሥራ ማህበር የ2016 ዓ.ም የሂሳብ እንቅስቃሴውን ህጋዊ የኦዲት ሥራ ፍቃድ ያላቸውን ባለሙያዎች በጨረታ በማወዳደር ኦዲት ማሠራት ይፈልጋል፡፡
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ህዳሴ ቦሌ ሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ ህብረት ሥራ ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ህዳሴ ቦሌ ሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ ህብረት ሥራ ማህበር የ2016 ዓ.ም የሂሳብ እንቅስቃሴውን ህጋዊ የኦዲት ሥራ ፍቃድ ያላቸውን ባለሙያዎች በጨረታ በማወዳደር ኦዲት ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት ማሟላት የምትችሉ ህጋዊ የኦዲት ፍቃድ ያላችሁ ከ29/2/2017 ዓ.ም እስከ 6/3/2017 ዓ.ም ባሉት ሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን 100 ብር (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እና ጨረታው የሚከፈትበትም 9/3/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች በቦታው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው የሚከፈትና አሸናፊው የሚለይ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
መስፈርቶቹ ፡-
- የሥራ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፣
- በዘመኑ /2016 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣
- ህጋዊ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ፣ TIN NO፤ VAT እና ማህተም ያለው፣
- የAABE ድርጅት ብቃት ማረጋገጫ ያለው ያላት፤
- የማህበራትን ሂሳብ ኦዲት በማድረግ ልምድ ያለው/ያላት ቢሆን ይመረጣል፡፡
- 2% ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል/የምትችል፣
- የህብረት ሥራ ማህበራት የኦዲት ሥልጠና የወሰደ/ች ቢሆን ይመረጣል፡፡
- ሥራውን በመሥራት ቢያንስ 2 ባለሙያዎችን መድቦ ማሠራት የሚችል/የምትችል
ተጫራች ግለሰቦችና ድርጅቶች ከላይ በቀረበው የጊዜ ገደብ መሰረት በለሚራ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ ዘጠኝ አጠገብ በሚገኘው የማኅበሩ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻን፣
የማህበሩ ሥራ አመራር ቦርድ
ስልክ 09 13 45 63 13
ህዳሴ ቦሌ ሸማቾች ኃላ/የተ/የህ/ስ/ማህበር
