በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ለክልሉ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ለክልሉ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የተሽከርካሪ አይነት |
ብዛት |
|
1 |
Station wagon 9 seat |
1 |
|
2 |
Double cabin pick up |
2 |
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣
- የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት /Tin Number/ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸው የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት፣
- ማንኛውም ተጫራች የንግድ ፍቃዱን በማቅረብ ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ሆሳዕና በሚገኘው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የግዥና ዋጋ ጥናት ዳይሬክቶሬት በመቅረብ የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ክፍት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ጋዜጣው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው 30ኛ ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የግዥና ዋጋ ጥናት ዳይሬክቶሬት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው በጋዜጣ የሚውልበት የመጨረሻ ቀን በዓል፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች 300,000/ሶስት መቶ ሺህ/ ብር የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው።
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910928986 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት
ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
/ሆሳዕና/
