Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Road Works Enterprises (ARWE) (የአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት)
  • Address አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0583203578
  • Website
  • Deadline04 Dec 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት የ2015 በጀት አመት ሂሳብ በFRS ሂሳቡን በተፈቀደላቸው አዲተሮች አዲት ለማስደረግ ይፈልጋል። በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላል።

Amhara Road Works Enterprises (ARWE) (የአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት)


በድጋሚ  የወጣ  የሂሳብ  ምርመራ  (የኦዲት)  አገልግሎት  ግዥ

ብሄራዊ  ግልጽ  ጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ሰነድ  ቁጥር 06/17

የአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት የ2015 በጀት አመት ሂሳብ በFRS ሂሳቡን በተፈቀደላቸው አዲተሮች አዲት ለማስደረግ ይፈልጋል። በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላል።

  1. የድርጅቱን ሂሳብ በIFRS መሰረት አዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው፣
  2. የዘመኑን ግብር ከፍሎ የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ
  3. ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነምግባራቸውን በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪው አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት ወይም ከኢትዮጵያ ሒሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ (ተቋሞቹ የሚሰጡ ከሆነ)
  4. የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፣
  5. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 ቀናት በድርጅታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከድርጅቱ ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመግዛት መጫረት ይቻላል፡፡
  6. ከብር 200.000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለሚሆን ግዥ ተወዳዳሪዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  7. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታከሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ "የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ" እና "የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ማስያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያው ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያው ሰነድ ካለበት ፖስታ ውስጥ አስጉበቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የስራ ቀናት ውስጥ ዋናው ቢሮ ግዥ ክፍል ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ ከላይ በተገለጸው መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል::
  8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት በድርጅቱ ግዥ ክፍል ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ጨረታው ይከፈታል። 20ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን 8፡30 ይከፈታል።
  9. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡-

  • የአብክመ የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር በቁጥር መልድአ/767/3/መጉ1 በቀን 20/05/2016 በተጻፈ ደብዳቤ በክልሉ ተቀባይነት ያላቸው የሂሳብና ኦዲት ሪፖርት የሚያዘጋጁ ባለሙያዎች ዝርዝር ማሳወቁ ይታወሳል:: ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ እየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ተለዋጭ መመሪያ ካልተላለፈ በስተቀር የምናወዳድረው በዝርዝሩ መሰረት ወይም ፈቃዳቸውን በአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ያሳደሱትን ብቻ እንደሚሆን ይታወቅ::
  • ተጨማሪ ማብራሪያ ከአስፈለገ በስልከ ቁጥር 0583203578 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል።

 

የአማራ  መንገድ  ስራዎች  ድርጅት

ባ/ዳር

Save Tender