በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ግብርና ቢሮ ለእንስሳትና ዓሳ ሴክተር ልማት አገልግሎት የሚሆን 35 ኩንታል መጫን የሚችል ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ግብርና ቢሮ ለእንስሳትና ዓሳ ሴክተር ልማት አገልግሎት የሚሆን 35 ኩንታል መጫን የሚችል ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የተሽከርካሪው አይነት |
ብዛት |
|
1 |
35 ኩንታል መጫን የሚችል ተሽከርካሪ |
2 |
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ
- የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት/Tin Number/ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸው የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት
- ማንኛውም ተጫራች የንግድ ፍቃዱን በማቅረብ ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ሆሳዕና በሚገኘው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የግዥና ዋጋ ጥናት ዳይሬክቶሬት በመቅረብ የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት አየር ላይ ይውላል።
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ጋዜጣው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው 30ኛ ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የግዥና ዋጋ ጥናት ዳይሬክቶሬት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ30ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው በጋዜጣ የሚውልበት የመጨረሻ ቀን በዓል፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች 200,000/ሁለት መቶ ሺህ/ ብር የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልከ ቁጥር 0910928986 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት
ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
/ሆሳዕና/
