Tender Detail

Tender Details

  • Company Jimma University (ጅማ ዩኒቨርስቲ)
  • Address Jimma , Oromia Region , Ethiopia, Phone: 251471123895
  • Websitehttps://ju.edu.et/
  • Deadline03 Dec 2024, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Health Care, Medical Industry

የጅማ ዩኒቨርሲቲ በገቢ ማመንጫና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት ስር ለሚተዳደረው ለሞዴል ፋርማሲ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መድሐኒቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡

Jimma University (ጅማ ዩኒቨርስቲ)


የጨረታ  ማስታወቂያ

የጅማ ዩኒቨርሲቲ በገቢ ማመንጫና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት ስር ለሚተዳደረው ለሞዴል ፋርማሲ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መድሐኒቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡

ሎት ፡- የመድሃኒት ግዥ

በዚሁ መሠረት በጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ደኖርበታል ፡፡

  1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የተለያዩ የመድኃኒቶች አቅርቦት ጋር አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ፤ የገንዘብ ሚኒስቴር የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት እና ወቅታዊ የግብር ግዴታዎችን እየተወጡ ያሉና በጨረታው ተካፋይ ለመሆን እንዲችሉ የሚገልጽ የሀገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር ) በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ዋስትና (Bid bond) ጋራንቲ እንዲሁም በማይክሮ የተደራጁ ከሆነ ካደራጃቸው ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የጨረታ ዋስትና በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ፋርማሲ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል ::
  3. ተጫራቾች ለአሸነፉባቸው የተለያዩ የመድኃኒቶች አቅርቦቱን የሚፈጽሙት በራሳቸው የትራንስፖርት ወጭ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ሞዴል ፋርማሲ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ማናቸውንም የመንግስት ታከስና የግብር ግዴታዎችን በሚያቀርቡት የእያንዳንዱን የማወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውስጥ አካተው ማቅረብ አለባቸው ::
  5. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ፋርማሲ ቢሮ ወይም በአዲስ አበባ ልደታ ብስራት ሆቴል ከፍ ብሎ 100 ሜትር ላይ የሚገኘው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ጽ/ቤት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በግንባር መረጃዎችን ይዞ በመቅረብ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

የጨረታው ሠነድ የሚዘጋውና የሚከፈተው

የጨረታ ሰነድ የመድኃኒት ግዥ እስከ ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ጅማ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ገቢ ማመንጫና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ:: ጨረታው የሚከፈተው በዛው ዕለት ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት በጅማ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫና ኢንቨስትመንት ዳይሬከቶሬት ቢሮ የሚከፈት ይሆናል፡፡

የበለጠ መረጃ ቢያስፈልግዎት በስልክ ቁጥር 0471116912 : 0471119979 ወደም 0111550621 አዲስ አበባ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

* ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

 

ጅማ  ዩኒቨርሲቲ

Save Tender