በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች/ መኪናዎች፤ ትራክተሮች እና ሞተር ሳይክሎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች/ መኪናዎች፤ ትራክተሮች እና ሞተር ሳይክሎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርባችሁ መወዳደር ትችላላችሁ።
* ሎት - 1 መኪናዎች
* ሎት - 2 ትራክተሮች
* ሎት - 3 ማሽነሪዎች
* ሎት- 4 ሞተር ሳይክሎች
- ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት አድራሻ በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት እና በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
- በተሽከርካሪዎች ጨረታ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም እና የተጫራቾች መመሪያ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በተናጠል፡- ሎት - 1 መኪና ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ፣ ሎት - 2 ትራክተር ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/፣ ሎት- 3 ማሽነሪ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ እና ሎት 4- ሞተር ሳይክል ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመክፈል በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩትን ተሽከርካሪዎች በሎት፣ በተናጠል ወይም በድምር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመነሻ ዋጋ 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ መሙያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ማስታወቂያ ይህ የጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታ አንድ ዋና /Original/ እና ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በፖስታ ታሽጎና እንደገና ሁለቱም በአንድ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በማሽግ ቢሮ ቁጥር 16 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ፣ በአሃዝና በፈደል በመጻፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለባቸው፤ ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ከአንድ በላይ ተሽከርካሪ መጫረት ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው አስራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ5፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪዎች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ በተገለጸ በ10/ አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው፤ ሆኖም በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ገዢው ካላነሳ ለሚደርሰው ለማንኛውም ችግር ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ከመንግስት የሚፈለግ ግብርና ቀረጥ በሻጩ የሚሸፈን ይሆናል።
- አሸናፊው ተጫራች የተሽከርካሪ ስም ማዘዋወሪያ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች በሙሉ በአሸናፊው ይሸፈናል።
- ተጫራቾች የመነሻ ዋጋ እና የዋጋ ማቅረቢያ የጨረታ ሰነድ አካል ሲሆን ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘ ነው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-37-23-10-26/ 09-10-45-46-56/ 09-16-67-34-83/
09-54-23-15-28 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
