የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የፀረ-ተባይ መቆጣጠሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሶስት (3) ዓመት በሚቆይ የኮንትራት ስምምነት ለማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር -SSNT-T498
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የፀረ-ተባይ መቆጣጠሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሶስት (3) ዓመት በሚቆይ የኮንትራት ስምምነት ለማሰራት ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-
- በአገልግሎቱ ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና TIN ምዝገባ ወረቀት ያለው፤ VAT ተመዝጋቢ የሆነ፤ አንድ (1) ዓመትና ከዚያ በላይ የሰራ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (100.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277 (E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T498 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (Scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም የባንከ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማቅረብ ይኖርበታል:: ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ከባንክ የሚቀርብ ሁኔታዊ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው:: ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:15 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ-
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩኘ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ወ/ሮ ሰላማዊት አባተ
ስልክ ቁጥር 011-517- 4258
ኢ-ሜል : selamawita@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
