በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ውስጥ የሚገኘው የቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ት/ጽ/ቤት የቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ውስጥ የሚገኘው የቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
- የደንብ ልብስ፣
- አላቂ የህክምና እቃዎች፣
- አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- የጽዳት እቃዎች፣
- ሌሎት የእጅ መሳሪያዎች፣
- አላቂ የትምህርት እቃዎች፣
በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች:-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉበት፤ የቫት ከፋይ ሰርተፍኬት ያላቸው፤ በገንዘብና በኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የዕቃና አገልግሎት ግዥ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ:
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ የጨረታውን አጠቃላይ ዋጋ 2 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ከላይ ለተዘረዘሩት እቃዎች ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በግልጽ በመሙላትና በኤንቨሎፕ በማሸግ ዋናውንና ኮፒውን ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 7 ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው የሚቆየው ማስታወቂያው ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ናሙና ለተጠየቃቸው ዕቃ ሁሉ ናሙና ማቅረብ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያው በወጣበት 10ኛ ቀን ላይ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይዘጋና በማግስቱ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ሂደት ቅሬታ ያለው አካል ጨረታው ከተከፈተ እስከ 3 ቀን ድረስ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል።
- የጨረታው አሸናፊ ላሸነፈው እቃ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መዋዋል ግዴታ ሲሆን አልዋዋልም ቢል ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ባቀረቡት ናሙና መሰረት አሸናፊ ሲሆኑ ያሸነፉበት ዕቃ በናሙናው መሰረት የማቅረብ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ካላቀረቡ በህግ ይጠየቃሉ፡፡
- ተጫራቾች ስቶክ /ስቶር/ ባለ እቃ መወዳደር ሲኖርባቸው እቃው ገበያ ላይ የለም ወይም ዋጋ ጨምሯል በሚል ምክንያት አልዋዋልም በሚሉ ተጫራቾች ላይ ት/ቤቱ አግባብ ባለው ህግ የሚጠይቃቸው ይሆናል።
- ተጫራቾች አሸናፊ ሲሆኑ ያሸፉበትን ዕቃ የጨረታ ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት ማስያዝ አለባቸው::
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 011-4-42-60-36 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ሳሪስ የገበያ ማዕከል ሬይስ ኢንጂነሪንግ ጀርባ ቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ት/ጽ/ቤት
የቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
