አባይ 1ኛ ደረጃ ከፍተኛ አገር አቋራጭ አውቶብስ የግል ባለንብረቶች ማህበር ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ውጭ ዲተሮችን የ2013 እና የ2014 በጀት ዓመት ሂሳብ ማስመርመር ይፈልጋል።
አባይ 1ኛ ደረጃ ከፍተኛ አገር አቋራጭ አውቶብስ የግል ባለንብረቶች ማህበር
የውጭ የሂሳብ ኦዲት ጨረታ
ማስታወቂያ
አባይ 1ኛ ደረጃ ከፍተኛ አገር አቋራጭ አውቶብስ የግል ባለንብረቶች ማህበር ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ውጭ ዲተሮችን የ2013 እና የ2014 በጀት ዓመት ሂሳብ ማስመርመር ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ተጫራቾች፡-
- አውቅና ያላቸው ከዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የተሰጣቸው: በመስክ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የህዝብ ትራንስፖርት ማህበራትን ሂሳብ በመመርመር የስራ ልምድ ያላቸው፣
- የማህበሩን ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችሉትን ዋጋ መጠንና ስራውን አጠናቅቀው የሚያስረክቡበትን የጊዜ ገደብ መጥቀስ ይኖርባቸዋል፡፡
- በንብረት ቆጠራ ወቅት በታዛቢነት ሊገኙ የሚችሉ፤
- ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረቡ፤
- በአጭር ጊዜ ስራውን አጠናቀው ጠቅላላ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተወዳዳሪዎች ዋጋ ከማቅረባቸው በፊት የማህበሩን ሂሳብ ሰነድ አዲስ ከተማ መናኻሪያ ቢሮ ቁጥር 6 በሚገኘው የማህበሩ የፋይናንስ ቢሮ መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ባለው ሰአት፤ ከ7፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት በተጨማሪ ቅዳሜ ከ2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣ በ8ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ ስራ አስኪያጅ ቢሮ ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
ማህበሩ ለስራው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ዋና መናኻሪያ ቢሮ ቁጥር 6
ስልክ ቁጥር፡- 0112732026/0911887071/0911763389
አባይ 1ኛ ደረጃ ከፍተኛ አገር አቋራጭ አውቶብስ
የግል ባለንብረቶች ማህበር
