Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ
  • Address ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0462121127
  • Website
  • Deadline23 Nov 2024, 12:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Electrical And Electromechanical

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለቢሮ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎችን ግዥ በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለቢሮ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎችን ግዥ በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት፡-

  • በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው
  • የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ቴክኒካል ኦሪጅናል 1 እና 2 ፎቶኮፒ፤ ፋይናንሻል ኦሪጅናል 1 እና 2 ፎቶ ኮፒ በA4 ወረቀት ለአንድ ወረቀት አንድ ኮፒ ብቻ በማድረግና በማዘጋጀት እያንዳንዱን በተናጠል በፖስታ በማሸግ በፖስታው ውጭ የሰነዱን ዓይነት ኦሪጅናል ወይም ኮፒ መሆኑን በመፃፍ ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር )ብቻ CPO ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ጉዳይ የተዘጋጀ የዕቃዎቹ ዝርዝር መግለጫዎችን የያዘ ሰነድ /Specification/ ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬከቶሬት በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) ብቻ ከፍለው በመግዛት ሰነዱ ላይ በመፈረም እና የድርጅታችሁን ማህተም በማሣረፍ ለዕቃዎቹ የሚያቀርቡትን ዋጋ በድርጅቱ በዋጋ መሙያ ፎርም ላይ በመሙላት ቫትን ያካተተ ስለመሆኑ በመግለፅ ፖስታውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 16ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን እንዲያስገቡ እያሳሰብን ጨረታው 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፡- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

ለበለጠ መረja በስልክ.ቁ 0462121127/0968625500

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
MSF Belgium Ethiopia Mission Tender for Supply of Various Types of Stabilizers (Tender Ref. ET121 &...

READ MORE