Tender Detail

Tender Details

  • Company Children Cross Connection (CCC) (ችልድረን ክሮስ ኮኔክሽን)
  • Address ወላይታ ሶዶ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0465512816
  • Website
  • Deadline14 Nov 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cargo Vehicle

ችልድረን ክሮስ ኮኔክሽን አገልግሎቱን የጨረሰ መኪና ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል፡፡

Children Cross Connection (CCC) (ችልድረን ክሮስ ኮኔክሽን)


ያገለገለ  መኪና  ሽያጭ

ጨረታ ማስታወቂያ

ችልድረን ክሮስ ኮኔክሽን አገልግሎቱን የጨረሰ መኪና ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል፡፡

ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብር ብቻ በመከፈል ወላይታ ሶዶ ከተማ ከድርጅቱ ቢሮ ወይም አዲስ አበባ ከሚገኝ ወኪል መውሰድ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም

  1. ተጫራቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት የሚሸጠውን መኪና አዲስ አበባ ቀርበው መመልከት ይችላለ፡፡
  2. ተጫራቾች ለሚገዙት መኪና የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታው ዶከመንት ውስጥ በተዘጋጀው የመጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት በታሽገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አስገብተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ ችልድረን ክሮስ ኮኔክሽን ወላይታ ሶዶ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ግቢ ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት መኪና የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ /በችልድረን ክሮስ ኮኔክሽን/ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/ሲፒኦ/ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ጋር በታሸገ ፖስታ ውስጥ አብሮ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4፡30 ሰዓት በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን አሸናፊው ወዲያው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ታሳቢ በማድረግ ቀሪውን ገንዘብ በ10 ቀናት ውስጥ ከፍለው ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው:: በጨረታው አሸንፈው ከፍለው ለማይወስዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል:: የጨረታ አሸናፊዎች መኪኖቹን የማጓጓዣ ወጪዎችንና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎችን ይሸፍናሉ፡፡
  5. በጨረታው ለሚሸነፉት ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ/ቢድቦንድ/ የጨረታ አሸናፊው ሙሉ ክፍያውን እንደፈጸመ የሚመለስላቸው ይሆናል፡፡

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። አድራሻ፡ ወላይታ ሶዶ በድርጅቱ ዋና ግቢ ስልክ፡ 0465512816/0911720913

ችልድረን ክሮስ ኮኔክሽን

 

Save Tender