Tender Detail

Tender Details

  • Company የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (Amhara Building Works Construction Company)
  • Address , Phone: 0583217806
  • Website
  • Deadline20 Nov 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የአማራ ህንፃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የ2016ዓ.ም በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች አዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡

የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (Amhara Building Works Construction Company)


የሂሳብ  ምርመራ  (የኦዲት) አገልግሎት ግዥ

ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ሰነድ ቁጥር 07/2017

የአማራ ህንፃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የ2016ዓ.ም በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች አዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላል፡፡

  1. የድርጅቱን ሃሳብ በFRS መሰረት ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር Tax Identification Number (TIN) ያለው፣
  2. የዘመኑን ግብር ከፍሎ የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ፣
  3. ተጫራቶች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪው አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት እና ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፣ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል አዲተሮች ማህበር እንዲሁም ከዚህ በፊት አዲት ካደረጋቸው የልማት ድርጅቶች የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት ፤
  4. የሂሣብ ምርመራው (አዲቱ) በበባህርዳር ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፣
  5. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በጽ/ቤታችን ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አመልድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍሎ ከድርጅቱ በመግዛት መጫረት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የቴክኒክ መወዳደሪያ ሰነድ” ፣ “የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ” እና “የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ማስያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያው ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያው ሰነድ ካለበት ፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የስራ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር  107 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ከላይ በተገለጸው መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል::
  7. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያና መክፈቻ ባ/ዳር ከተማ በአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቀበሌ 11 ኮብል አክሲዮን ማህበር ፊት ለፊት ወደ ዲያስፖራ በሚወስደው መንገድ በሚገኘው የድርጅቱ ህንጻ ሲሆን የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን- ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ መዝጊያ ቀን በ15ኛው ቀን 8፡00 ይዘጋና በዚያኑ ቀን 8፡30 ይከፈታል፡፡15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ በዚያውኑ ቀን 8፡00 ተዘግቶ 8:30 ይከፈታል፡፡
  8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር ፡- 0583217806/0918292107

 

የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት

ባህርዳር

Save Tender