የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ኮምፒዩተር እና ተያያዥ የቢሮ ኤሌከትሮኒክስ መሣሪያዎች እንዲሁም የቪዲዮ ኮንፈረንስ መሣሪያዎችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴክኒካል መስፈርት መሠረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
ኮምፒዩተር እና ተያያዥ እቃዎችን ለመግዛት የወጣ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/06/2017
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ኮምፒዩተር እና ተያያዥ የቢሮ ኤሌከትሮኒክስ መሣሪያዎች እንዲሁም የቪዲዮ ኮንፈረንስ መሣሪያዎችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴክኒካል መስፈርት መሠረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ፣ የቫት ተመዝጋቢ፤ ቲን እና ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ በሚገኘው ፋፋ የምግብ አ.ማ ጀርባ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 110 ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ 2% በሲፒኦ ወይም በባንከ ጋራንቲ (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታው ዋጋ ለ90 ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል። ጨረታው ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
ስልክ ቁጥር፡- 011470-90-95 ወይም
0114-423608
0114-421312
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
