Tender Detail

Tender Details

  • Company በሰሜን ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ፍ/ቤት ደብረ ብርሃን
  • Address በባሶና ወራና ወረዳ ፍ/ቤት ደ/ብርሃን ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 ደብረ ብርሃን ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-890-0086
  • Website
  • Deadline20 Nov 2024, 5:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cloth And Shoes

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ለባሶና ወራና ወረዳ ፍርድ ቤት እና ለቀይት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ፍ/ቤት ደብረ ብርሃን


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ቁጥር 1/2017

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ለባሶና ወራና ወረዳ ፍርድ ቤት እና ለቀይት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውል፡-

  1. የሰራተኞች ደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ
  2. የሰራተኞች ሸሚዝ
  3. የቆዳ ጫማ ውጤቶች
  4. ልዩ ልዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች
  5. የጽዳት እቃዎች
  6. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  7. ልዩ ልዩ የሚሰሩ እና የተዘጋጁ ቋሚ እቃዎች
  8. ልዩ ልዩ የኤሌከትሮኒከስ እቃዎች ጥገና እና
  9. የቢሮ ቋሚ እቃዎች ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ወይም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፣
  3. የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡-
  • ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከ27/2/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ቀናት ከባሶና ወራና ወረዳ ፍ/ቤት ደ/ብርሃን ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 የአገልግሎቱን ዓይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች በተራ ቁጥር ከ 1 እስከ 9 የተጠቀሰውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 /አምሳ ብር/ ብቻ ለእያንዳንዳቸው በመክፈል ከባሶና ወራና ፍ/ቤት ደ/ብርሃን ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የሚያቀርቡበትን የአገልግሎት ጠቅላላ ዋጋውን /ቫት/ ጨምሮ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ፖስታ በጥንቃቄ ታሽጐ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት በባሶና ወራና ወረዳ ፍ/ቤት ደ/ብርሃን ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ቀርበው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ጨረታው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቁጥር 11 በይፋ ይከፈታል፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  • ናሙና እንዲቀርብ የተጠየቁትን እቃዎች ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
  • ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-890-0086 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡
  • አሸናፊ ተጫራቾች እቃውን ለባሶና ወራና ወረዳ ፍ/ቤት ናሙና የተጠየቀውን በናሙናው መሰረት ናሙና የሌለውን በውሉ መሰረት በማቅረብ ገቢ ያደርጋል፡፡

 

በሰሜን ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ፍ/ቤት

ደብረ ብርሃን

 

Save Tender