Tender Detail

Tender Details

  • Company የአርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
  • Address አርባምንጭ ከተማ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline24 Nov 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

የአርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለሼቻ ምድብ ችሎት ሕንፃ ግንባታ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

የአርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የአርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለሼቻ ምድብ ችሎት ሕንፃ ግንባታ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ፡

  1. ህጋዊ ምዝገባ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑ ኮንስትራከሽን ደረጃ 9 ፈቃድ ያሳደሳችሁ፤
  2. ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ እንዲችሉ ከሚመለከታቸው ኮንስትራክሽን ዘርፍ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የ2016 ዓ/ም ንግድ ሥራ ፈቃድ ያሳደሳችሁ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያላቸው ::
  4. ተጫራቾች ለጨረታው ሰነድ የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚጠናቀቅበት 21ኛ ቀን ድረስ ተከታታይ በሥራ ሰዓት በአ/ም/ከ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ግ/ፋይ/ን/አስ/ር ቢሮ ቁጥር 10 መውሰድ ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 25.000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ብቻ በባንክ ብር/ የተመሰከረለት CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
  6. ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ኦሪጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 21ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፣ የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይሆናል።
  7. ጨረታው የሚከፈተው በ22ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፣ ቀኑ የበዓል ቀን ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  8. የጨረታው ማስከበሪያው CPO በአሪጅናል ዶክመንት ውስጥ መሆን ይኖርበታል።
  9. ከዚህ በፊት በአፈፃፀማቸው ማስጠንቀቂያ የተፃፈባቸው ተጫራቶች መወዳደር አይችሉም።
  10. የአቅራቢነት የኤሌክትሪክ ኦንላይን ምዝገባ ፕሪንት አውት (EPG) ማቅረብ የሚችሉ።
  11. ሁሉም ተጫራቾች የግንባታ ቁሳቁሶችን በራሳቸው አጓጉዘው እንደሚገነቡ በግልጽ የተረዱ መሆን አለባቸው።
  12. ማንኛውም ተጫራቾች ከውድድሩ በፊት የስራ ሳይቱን ሆነ ሥራውን በራሱ ወጪ ተንቀሳቅሶ ስለ ስራው ይዘትና የስራውን ቦታ በማየት ሁኔታውን ካረጋገጠ በኋላ ነጠላ ዋጋውን መሙላት አለበት።
  13. ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት ውስጥ የግንባታ ውል ገብተው እና ሥራውን ተረክበው ግንባታውን ያላስረከቡ ተጫራቾች በጨረታ መወዳደር አይችሉም።
  14. ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ አለው፡፡

 

የአርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት

Save Tender