በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብና መምሪያ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ ግዥ፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ፣ ሎት 3 ጫማ፣ ሎት 4 የተዘጋጀ ልብስ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብና መምሪያ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ ግዥ፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ፣ ሎት 3 ጫማ፣ ሎት 4 የተዘጋጀ ልብስ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆንም ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሣተፍ ይችላል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
- የእቃው መጠን 200,000.00 ብር በላይ ከሆነ የቫት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ለእቃ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በኋላ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ይዘጋና በዛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በታሸገ ፖስታ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የዕቃው አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእቃ ግዥ ብር 300 ብር በመክፈል ከግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 26 የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለእቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጨረታ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገን/ኢኮ/ ትበብር ጽ/ቤት ቁጥር 34 ለእቃ ግዥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 34 የጨረታ ማስታወቂያው ከወጠበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው ቀን 4:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻውና መዝጊያው ከመንግስት ስራ ቀን ውጪ ወይም በበዓል ቀን ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡
- ውድድሩ በጥቅል (በሎት) ስለሆነ ተጫራቾች በከፊል መሙላት አይቻልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የሚገዛቸውን እቃዎች የትራንስፖርትም ሆነ ሌሎች ወጪዎችን አይሸፍንም፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 35 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልከ ቁጥር 033-6-64-03-71/ 033-6-64-13-36 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
