Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ
  • Address ሀዋሳ ከተማ ከሚገኘው ቀድሞ ደቡብ መንገዶች ባለስልጣን ጎን ፡ ሲዳማ ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: +251916035592
  • Website
  • Deadline18 Nov 2024, 4:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ የድርጅቱን ሂሳብ የውጭ ኦዲተሮችን በጨረታ አወዳድሮ የድርጅቱን ሂሳብ ኦዲት ማስደረግ ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

የሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ


የውጭ ኦዲት የጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ የድርጅቱን ሂሳብ የውጭ ኦዲተሮችን በጨረታ አወዳድሮ የድርጅቱን ሂሳብ ኦዲት ማስደረግ ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

መስፈርቱም:-

  • ከኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የታደሰ የሙያ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል።
  • በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው።
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታ የሚወዳደሩበትን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  • ማንኛውም ተጫራች 2% በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም ከስድስት ወር ያላነሰ ጊዜ ያለው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ቢድ ቦንድ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  • ጨረታው በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  • ከላይ በዝርዝር የተቀመጠውን መስፈርቶች የሚያሟላ ኦዲተር በዚሁ ሥራ ላይ መወዳደር የሚቻል መሆኑን እየገለጽን ያልተሟላ መረጃ ለሚያቀርብ ኦዲተር ከውድድር ዉጪ ይሆናል።

ማሳሰቢያ፡- ከላይ በዝርዝር የተቀመጠውን መስፈርቶችን የሚያሟላ አዲተር በዚህ ሥራ ላይ መወዳደር የሚችል መሆኑና እየገለጽን ያልተሟላ መረጃ ለሚያቀርቡ ኦዲተር ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡

  • ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ ማብራሪያ፡- +251 916035592/+251 911806553

አድራሻ:- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሀዋሳ ከተማ ከሚገኘው ቀድሞ ደቡብ

መንገዶች ባሰስልጣን ጎን።

 

የሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ

Save Tender