Tender Detail

Tender Details

  • Company የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ
  • Address , Phone: 09-16-72-60-33
  • Websitehttps://wcu.edu.et/
  • Deadline12 Nov 2024, 12:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cargo Vehicle

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ በ2017 በጀት ዓመት ሎት፡-4 ለኃላፊዎች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ 15 ሰው የሚጭን ሀይሩፍ መኪና 2016 እና ከዛ በላይ ሞዴል መኪና ኪራይ እና የጭነት አገልግሎት የሚሰጥ አይሱዙ 2016 እና ከዛ በላይ ሞዴል መኪና ኪራይ ግዥ በሃገር አቀፍ ጨረታ አሳውጆ ህጋዊ ከሆኑ ነጋዴዎች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ


ሀገር  አቀፍ  ግልጽ  የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር  ዱ/ካ/03457/2017

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ በ2017 በጀት ዓመት ሎት፡-4 ለኃላፊዎች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ 15 ሰው የሚጭን ሀይሩፍ መኪና 2016 እና ከዛ በላይ ሞዴል መኪና ኪራይ እና የጭነት አገልግሎት የሚሰጥ አይሱዙ 2016 እና ከዛ በላይ ሞዴል መኪና ኪራይ ግዥ በሃገር አቀፍ ጨረታ አሳውጆ ህጋዊ ከሆኑ ነጋዴዎች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ፡-

ሎት 4 የሚወዳደሩ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-

  • በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ አግባብነት ያለው ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት፣
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/TN No/ ያለው/ያላት፤
  • የቫት ተመዝጋቢ የሆነ/የሆነች፣
  • በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/ትችል፣
  • የመኪናው ባለቤትነት ሊብሬ ማቅረብ የሚችል/ትችል፣
  • የተሸከርካሪው ወቅታዊ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ያለው/ያላት፣
  • ለተሸከርካሪው የሦስተኛ ወገንና ሙሉ ኢንሹራንስ ያለው ያላት፣
  • የተሽከርካሪው ወቅታዊ የቴክኒክ ምርመራ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/ትችል፣
  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ጨረታ በሃገር አቀፍ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 15 ተከተተይ ቀናት ውስጥ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ ከግዥና ንብረት አስ/ር ቢሮ በአካል በመቅረብ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ከተሰጠው መስፈርት ወይም የቴክኒከ ፍላጎት መግለጫ ውጪ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
  • ተጫራቾች እኩል ዋጋ ቢያቀርቡ አሸናፊው በዕጣ የሚለይ ይሆናል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታውን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
  • በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር የተገለጹ ዕቃዎች/አገልግሎት ዓይነት የማቅረቢያ ጊዜ በውል ስምምነት የሚገለጽ ሆኖ አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈውን ዕቃ/አገ/ት በራሱ ትራንስፖርት እስከ ዋቸሞ ዩኒቨርሲት ዱራሜ ካምፓስ ግቢ ድረስ ያቀርባል።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሎት፡-4 ለሀይሩፍ እና ለአይሱዙ መኪና ለእያንዳንዳቸው 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ባንከ ጋራንቲ ሌተር ደብዳቤ/ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በዱራሜ ካምፓስ ስም እዘጋጅተው ለብቻው በፓስታ በማሸግ ከኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የዕቃ የአገልግሎት ዝርዝር ነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ ተደርጎ በተሰጠው ዕቃ አገልግሎት ግዥ ዝርዘር ገጽ ወይም በራሳችሁ ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ቅደም ተከተሉን ሳያዛቡ በመሙላት የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በሁሉም ገጾች ላይ በማሳረፍ 1 /አንድ/ ኦርጅናል እና 2 (ሁለት) ፎቶ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ እስከ 16ኛው ቀን ፖስታውን በማሸግ በዋቸሞ ዩ/ዱ/ካ ግዥና ንብረት አስ/ር ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ግን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡ ጨረታው የታወጅበት ቀን በ18/2/2017 ዓ.ም የሚከፈትበት ቀን 3/3/2017 ዓ.ም ሆኖ አራቱም ሎቶች ከቀኑ 8:15 ሰዓት ላይ ታሽጎ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ቀን ከጠዋቱ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል ፡፡ ይሁን እንጂ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራቾቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፍላጎት አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም ፡፡
  • የጨረታው ውጤት ጨረታው ተገምግሞ እንዳለቀ በደብዳቤ፣ በፋክስ፣ በስልክ እና በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
  • ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የመልካም ሥራ አፈጸጸም ዋስትና (ውል ማስከበሪያ) በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ማንኛውም ተጫራች በውል ውስጥ የተካተቱትን ህጎች ማከበር አለበት፡፡
  • ተጫራቾች ከቫት ጋር በሚወዳደሩ ሎቶች ዋጋቸውን ሲሞሉ ከቫት ጋር ወይም ያለቫት ብለው መግለጽ አለባቸው:: ካልሆነ ግን የተሞላው ዋጋ ቫት 15% እንዳለ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
  • በዋጋ ማቅረቢያው ላይ የሚጻፈው ጽሑፍ በግልጽ የሚነበብ መሆን አለበት፡፡ ስርዝ ድልዝ ቢኖር ማስተካከያ በተደረገው ቦታ ላይ የድርጅቱ ህጋዊ ፊርማ መፈረም አለበት፡፡
  • ካምፓሱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ መረጃ፡- በ03/01/2017 ዓ.ም የወጣውን አዲስ ዘመን ጋዜጣ መመልከት ይችላሉ፡፡

በስልክ ቁጥር፡- 09-16-72-60-33/09-20-46-91-21 ደውሎ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ

Save Tender