በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን የቦንጋ ከተማ ፋይ/ ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በሎት 01 ኤሌክትሮኒክስ፣ በሎት 02 የከንቲባ ጽ/ቤት የቢሮ ጥገና እንዲሁም በሎት 03 የቦን/ከተ/ፋይ/ጽ/ቤት ንብረት ቤት /Store/ ግንባታ በዚህ ንግድ ዘርፍ ከተሰማሩት ድርጅቶች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
በደ/ምዕ/ኢትዮጵያ ሕ/ክ/መ/ካፋ ዞን የቦንጋ ከተማ ፋይናንስና ኢኮ/ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን የቦንጋ ከተማ ፋይ/ ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በሎት 01 ኤሌክትሮኒክስ፣ በሎት 02 የከንቲባ ጽ/ቤት የቢሮ ጥገና እንዲሁም በሎት 03 የቦን/ከተ/ፋይ/ጽ/ቤት ንብረት ቤት /Store/ ግንባታ በዚህ ንግድ ዘርፍ ከተሰማሩት ድርጅቶች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ለመሳተፍ የሚትፈልጉ አመልካቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- ግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ገቢዎች ባለስልጣን የቲን ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በ2016 ዓ/ም የሰሩበት የመልካም ስራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በሎት 02 እና 03 የተጫራቾች ደረጃ BC 5 እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፡፡
- የጨረታው ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ ቁጥር 3 መግዛት ይችላል፡፡
- በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፁ መረጃዎች በጨረታ ዶክመንት ላይ ያሉት ገዥ ይሆናሉ።
- የጨረታ ሰነዱ በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከአንድ ኦርጅናል ቴክኒካል ና ፋይናንሻል እንዲሁም ከአንድ ኮፒ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ተዘጋጅቶ የሚቀረብ ሲሆን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል::
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻ ሰዓት ያለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉለውም፡፡
- የጨረታው መከፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሁሉም ሎቶች 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በፖስታ ታሽጎ የሚገባውም ሆነ የሚከፈተው በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይቸላል፡፡
የቦንጋ ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት
