የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የበሬና የበግ ሥጋ፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች እንዲሁም የታሸገ ውሃ የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/17
የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የበሬና የበግ ሥጋ፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች እንዲሁም የታሸገ ውሃ የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚወዳደሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው::
በዚህም መሰረት፡-
- ተጫራቾች በዘርፋ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ የምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን ሲሆን ሰነድ የሚሸጠው በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ አዲስ አባባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ከፍል በመክፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 አቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ፖስታውን ፋይናንሻል እና ቅድመ መገምገሚያዎችን /ቴክኒካል ሰነድ/ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በየሎቱ /የጨረታ ሰነድ ላይ/ የተገለፀውን ብር በሲፒኦ ወይም በባንከ ዋስትና ከቴክኒካል ህጋዊ ሰነዶች/ ኦርጅናል ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ይህ የጨረታ ደብዳቤ ወጪ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውልና በ15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይሆናል፡፡
- ሆኖም የተጋበዙት ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ የጨረታውን ሰነድ ሞልተው ከመለሱ የመከፈቻ ቀኑን ሳይጠብቅ የተጋበዙ ድርጅቶችን በማሳወቅ ሊከፈት ይችላል፡፡
- ተጋብዘው ፍቃደኛ በመሆን ሰነድ የመለሱ ድርጅቶች በተሰጣቸው ናሙና መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንደአስፈላጊነቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ስልክ ቁጥር 0116 454147/0116-453598/0118-694931 ከሳህሊተ ምህረት ማርያም ቤ/ከርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ
የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት
