በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ በቢሮ፣ ዞን፤ ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና ሞተር ሳይክሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የኦሮሚያ ብሔራዊ
ግልፅ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 05/2017
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ በቢሮ፣ ዞን፤ ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና ሞተር ሳይክሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ኅዳር 11/2017 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤
- የኤጀንሲው አድራሻ፦ አዲስ አበባ ሳርቤት ከፑሽኪን አደባባይ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ጨፌ ኦሮሚያ ጽ/ቤት ሳይደርስ ቤተልሔም ህንጻ ከሚገኘው የኤጀንሲው የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አንደኛ ፎቅ በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን 2ኛ ፎቅ የሽያጭ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30- 6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-11፡00 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
- የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ ኅዳር 1/2017 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-11፡00 ሰዓት ድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ኅዳር 13/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ኅዳር 13/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡30 ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡45 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ መነሻ ዋጋ 20% /ሃያ ከመቶ/የጨረታ ማስከበሪያ C.P.O በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
CPO ለማሰራት
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ሌጀንሲ
Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 011-1-2368-27/011-1-23-68-21
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና
ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ
