የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የተለያዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና አገልግሎት የሚውል የሚኒባስ መኪና እና ባለአራት ተካፋች ፒክአፕ (Double Cabin Pickup 4 Door) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
Addis Ababa City Roads Authority (የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አአከመባ/ግብዓት/ቡ-2/001/2017
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የተለያዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና አገልግሎት የሚውል የሚኒባስ መኪና እና ባለአራት ተካፋች ፒክአፕ (Double Cabin Pickup 4 Door) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የስሪት ዘመን |
ዝቅተኛ የመጫን አቅም |
የጨረታ መለያ ቁጥር |
ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ |
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በብር |
|
1 |
ባለ አራት ተካፋች ፒክአፕ (Double Cabin Pickup 4 Door) |
በቁጥር |
145 |
> 2005 እ.ኤ.አ |
> 5 ሰው ሹፌሩን ጨምሮ |
አአከመባ/ ግብዓት/ ቡ-2/001/ 2017 |
60 ቀን |
ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 5፡00 |
ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡15 |
ለአንድ ሚኒባስ ለአንድ ፒክአፕ መኪና የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺ ብር/ |
|
2 |
ሚኒባስ መኪና
|
በቁጥር |
93 |
> 2005 እ.ኤ.አ |
> 12 ሰው ሹፌሩን ጨምሮ |
|
|
|
|
|
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ በመስኩ የተሰማሩበት የንግድ ስራ ፍቃድ፣ታክስ ክሊራንስ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ድረ-ገፅ ላይ (Online PPA Supplier list Registration Certificate) ላይ የተመዘገቡ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚዘጋበት ጊዜ ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ከባለስልጣኑ መ/ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 135 መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከ ተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለስልጣኑ መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሳር ቤት ፑሽኪን አደባባይ
ስልክ ቁጥር፡- 011-3-722825
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባስሥልጣን
