Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
  • Address ወላይታ ዞን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0465512100
  • Website
  • Deadline07 Nov 2024, 4:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Stationery Materials

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2017 ዓ.ም ከመደበኛ በጀት የጽ/መሣሪያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አሳውጆ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2017 ዓ.ም ከመደበኛ በጀት የጽ/መሣሪያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አሳውጆ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች፡-

    1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤
    2. ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
    3. ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የግዥ ከፍያ ንብረት አስ/ር ደጋፍ የሥራ ሂደት እየመጡ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።
    4. 5000 /አምስት ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ CPO ከሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
    5. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን የዋጋ ማቅረቢያ ሠነዶቻቸውን ኦርጅናሉን በፖስታ በማሸግ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ መጨረሻው ቀን ከቀኑ 10፡00 ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሠነዶቻቸውን ማስገባት አለባቸው፣ ጥራቱን በጥንቃቄ እናያለን ፡፡
    6. ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አሥራ አምስት/ ቀናት ከቀኑ 10፡00 ድረስ በሣጥኑ መጨመር አለባቸው፡፡ በዕለቱ 11፡00 ታሽጎ በሚቀጥለው ቀን ማለትም በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: በሠነዱ ከተባለው ውጭ ማቅረብ አይቻልም፡፡
    7. በጨረታው ሠነድ የተፃፈውን የዕቃ ዓይነት ተጫራቾች በትክክል መሙላት አለባቸው፡፡ የሚያቀርቧቸው ዋጋ ከቫት ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
    8. ያሸነፈ ተጫራች ዕቃውን እስከ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ፍርድ ቤቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን መለወጥ ሆነ መሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ በስልክ ቁጥር 0465512100 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት

የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት  

Save Tender