የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሠራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ አንድ ካስተር እና ሚኒባስ ለሠራተኞች ለሰርቪስ አገልግሎት የሚውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር ECC JB07/2017
የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሠራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ አንድ ካስተር እና ሚኒባስ ለሠራተኞች ለሰርቪስ አገልግሎት የሚውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ የንግድ የስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተሸከርካሪው ሙሉ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ካስተር ለ30 ሰው እና ከዚያም በላይ የመጫን አቅም ያለው በተጨማሪም ሚኒባስ 12 ሰው እና ከዚያ በላይ የመጫን አቅም ያለው ::
- የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ያለውና ግብር የገበረ የመንገድ ትራንስፖርት ቦሎ ያለው
- ተጫራቶች ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ፤ እሁድ ሙሉ ቀን እና በዓላት ቀን ክፍያና ስራ የሌለ መሆኑን አውቆ የሚጫረት ሆኖ መ/ቤቱ ለስራ ከፈለገው የሚሰራ፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳዱ 10,000.00 (አስር ሺህ ) ብር ጅግጅጋ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት ስም በንግድ ባንከ የተመሰከረለት (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት ጨምሮ በሚቆጠር 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለጨረታ ሰነዱ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ሰነዱን ከጅግጅጋ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ከገቢ ሒሳቦች ቡድን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናሻል ለየብቻ ከአንድ ኮፒ ጋር መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በጨረታው ቀን ብቻ እስከ ጠዋት 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላል፡፡
- ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 05 ጨረታው ይከፈታል 11ኛ ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን ጨረታው ይካሄዳል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ቀን የሚወዳደሩበት ተሽከርካሪ በአካል ወይም በቪዲዮ መቅረብ ይኖርበታል።
- አሸናፊው ድርጅት የማሽከርከር ፍቃድ ያለው ሾፌር ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻችን፡ በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ግዢና ፋይናንስ ቡድን 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 05 መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0904252386 ወይም 0921822252/0910208950
E-mail addres jijccarchive@gmail.com ወይም Getachewtakt@gmail.com
የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
