Tender Detail

Tender Details

  • Company Awash Bank S.C (አዋሽ ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115571107
  • Websitehttps://awashbank.com/am-et/
  • Deadline12 Nov 2024, 10:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cargo Vehicle

አዋሽ ባንክ አ.ማ ሲጠቀምባቸው የነበረውን 13 ተሽከርካሪዎች ባለብት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

Awash Bank S.C (አዋሽ ባንክ አ.ማ)


ያገለገሉ  ንብረቶች  የጨረታ

ማስታወቂያ

አዋሽ ባንክ አ.ማ ሲጠቀምባቸው የነበረውን 13 ተሽከርካሪዎች ባለብት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚቻል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።

  1. ስለ ጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር መረጃ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በሂሣብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ደረሰኙን አዋሽ ባንክ ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል የቢሮ ቁጥር M-101 በመቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሕዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማስገባት ይችላሉ፣
  2. እያንዳንዱ ተጫራች ለሚጫረትበት ተሽከርካሪ የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር ስም አሰርቶ ማስገባት ይኖርበታል፣
  3. ያለ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም
  4. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15%፣ የስም ዝውውር እና ተያያዥ የመንግስት ወጪዎችን ይከፍላል፤
  5. ንብረቶቹን ካዲስኮ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ጅምር ሕንጻ በአካል ቀርቦ በጨረታው ሰነድ ላይ በወጣው ፕሮግራም መሠረት መጐብኘት ይቻላል፤
  6. ጨረታው ሕዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል የቢሮ ቁጥር M-11 ውስጥ ይከፈታል፣ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፣
  7. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽሞ ንብረቶቹን መረከብ ይኖርበታል:: ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ለባንኩ ገቢ በማድረግ ጨረታው ይሰረዛል፣
  8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  9. ስለ ጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር ማብራሪያ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀን በፊት በስልክ ቁጥር 0115-303026/0115-303014 ደውለው መጠየቅ ይቻላል::
Save Tender