የአሮሚያ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ለ 2017 የበጀት አመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፡- CCTV Camera, Air Conditioner, Sound System በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Oromia Occupational Competency Assurance Agency (የኦሮሚያ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 1/2017
የአሮሚያ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ለ 2017 የበጀት አመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፡- CCTV Camera, Air Conditioner, Sound System በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ይህንን መስፈርት የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትጫረቱ ይጋብዛል፡፡
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡
- ተጫራቾች በዘርፉ መወዳደር የሚያስችል የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቲን (TIN) እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (BID BOND) ለሎት 1 ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ከጨረታ ማወዳደሪያ ኦሪጅናል ሰነድ ጋር በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የመዝጊያ ቀን ከ1፡00 ሰዓት ቀድመው ሰነዱን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ኤጀንሲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የጨረታው አሸናፊ እቃውን በ10 ቀን ውስጥ ማቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የሚገኝበት አድራሻ፡- አዳማ ወንጂ መንገድ የኦሮሚያ አዳሪ ት/ቤት ፊት ለፊት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 0222123599 /0911659749/ 0911069485 መደወል ይቻላል፡፡
በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ
የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ
