የአሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በ2017 ዓ.ም ለሚያካሂደው ለግንባታ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን፣ ገልባጭ መኪኖችን፣ አነስተኛ የመስክ መኪኖች፣ የውሃ ቦቴ መኪኖችን፤ ሎቤድ ፤ እንዲሁም ለግንባታ ሥራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች እና ተሽከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ኮርፖሬሽኑ ባዘጋጀው ቅጽ ላይ ዋጋውን ሞልተው እንዲያቀርቡ ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር NCB/OCC-095/2024
የአሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በ2017 ዓ.ም ለሚያካሂደው ለግንባታ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን፣ ገልባጭ መኪኖችን፣ አነስተኛ የመስክ መኪኖች፣ የውሃ ቦቴ መኪኖችን፤ ሎቤድ ፤ እንዲሁም ለግንባታ ሥራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች እና ተሽከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ኮርፖሬሽኑ ባዘጋጀው ቅጽ ላይ ዋጋውን ሞልተው እንዲያቀርቡ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- ከሥራው ጋር አግባብነት ያለው እና በ2017 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የሚፈለግባቸውን የመንግሥት የግብር ግዴታን ስለመወጣቱ የሚያመለከት ጊዜው ያላለፈበት ማስረጃ (ታክስ ክሊራንስ) ከሚመለከታቸው ገቢዎች ባለሥልጣን እና ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚገልጽ /TIN/ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ቃሊቲ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ከኮርፖሬት ግዥ ቡድን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የአገልግሎት አይነት ድርጅቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 28/2/2017 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በዚሁ ዕለት ማለትም በ28/02/2017 ዓ.ም ላይ ተዘግቶ 8:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር-0114390150
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
