ብርሃን ለሕፃናት የ2024 በጀት ዓመት የድርጅቱን የሃሳብ ሰነዶች በቂ ልምድ ባላቸው የተመሰከረላቸው የሂሳብ አዋቂዎች ማሠራት ይፈልጋል፡፡
ብርሃን ለሕፃናት
የጨረታ ማስታወቂያ
ብርሃን ለሕፃናት የማህበረሰብ ተሃድሶን መሰረት በማድረግ ሕፃናት ተኮርና የአካል ጉዳትን ያማከለ ሁለጉብ አገልግሎት ለመስጠት እ.ኤ.አ. በዲሴምበር 1997 የተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው:: በመሆኑም ድርጅቱ በአዲስ አበባ ከተማ በቀድሞው ወረዳ 22 በጥቂት ቀበሌዎች የተጀመረው ሥራ ዛሬ ላይ በአምስት ከልሎች ማለትም በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ፣ በደቡብ ወሎ ደሴ ከተማና ሐይቅ፡ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በቢሾፍቱ ከተማና በአድአ ወረዳ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሃዲያ ዞን፣ በአፋር ክልላዊ መንግሥት፡ በሲዳማ ክልል በሃዋሳ ከተማ እና በመልጋ ወረዳ ማህበረሰብን መሠረት ያደረጉ ፕሮግራሞችን ተግባራዊ በማድረግ ለአካል ጉዳተኛና በተለያዩ ምክንያቶች ለከፋ ችግር የተጋለጡ ሕፃናትን ለማብቃት የድርሻውን ጥረት የሚያደርግ መንግሥታዊ ያልሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን እ.ኤ.አ. የ2024 በጀት ዓመት የድርጅቱን የሃሳብ ሰነዶች በቂ ልምድ ባላቸው የተመሰከረላቸው የሂሳብ አዋቂዎች ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የኦዲት ሥራ መስራት ለምትፈልጉ ተጫራቾች:-
- የ2017 ዓ.ም. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
- የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈለ/ች/፤
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ሂሣብ የሠሩ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፣
- ሂሣብ ለመሥራት ከዋና ኦዲተር ወይም የሙያ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ፈቃድ ያገኘ መሆን ይኖርበታል፣
- የሂሣብ ሥራውን የያዙ መረጃዎች /ብርሃን ለሕፃናት ቢሮ በመምጣት ዝርዝር ሥራዎችን መመልከት ይችላሉ፣
- በአዲት ቦርድ ፍቃድ ያገኘ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል መሰረዝ ይችላል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ
የአገልግሎት ክፍያና ሂሣቡን የማስረከቢያ ቀናትን በመጥቀስ ሜክሲኮ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ መወዳደሪያችሁን እንድታቀርቡ እናሳስባለን፡፡
አድራሻ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ከፖሊስ ሆስፒታል ጀርባ አልሳም የመኖሪያ መንደር ፊት ለፊት ከኢትዮ
ፓናዲያን ዲያግኖስቲክስ አጠገብ ብርሃን ለሕፃናት ህንፃ፣
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
በስልክ ቁጥራችን 011-554-48-14/45 በሞባይል 092-272-09-20 ደውለው ይጠይቁ
ብርሃን ለሕፃናት
