Tender Detail

Tender Details

  • Company አማራ ደን ኢንተርፕራይዝ
  • Address ባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ, Phone: 0583202985
  • Website
  • Deadline27 Oct 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የ2016 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው አዲተሮች አዲት ለማስደረግ ይፈልጋል::

አማራ ደን ኢንተርፕራይዝ


የሂሳብ  ምርመራ (የኦዲት) አገልግሎት ግዥ

ጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የ2016 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው አዲተሮች አዲት ለማስደረግ ይፈልጋል:: በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላል፡፡

  1. የድርጅቱን ሂሳብ በIFRS መሰረት ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፤ የግብር መከፈያ መለያ ቁጥር (Tax identification Number TIN) ያለው:፡
  2. የዘመኑን ግብር ከፍሎ የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ፡፡
  3. ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪው እካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት እና ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር እንዲሁም ከዚህ በፊት ኦዲት ካደረጋቸው የልማት ድርጅቶች የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡
  4. የሂሣብ ምርመራው አዲቱ በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ።
  5. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በጽ/ቤታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር ከፍሎ ከድርጅቱ በመግዛት መጫረት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን ታክሱን ጨምሮ በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የቴከኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ፣ የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ማሲያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያው ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴከኒካል መወዳደሪያ ሰነድ ካለበት ፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የስራ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 13 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ከላይ በተገለጸው መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል::
  7. የጨረታ ሳጥኑ በ10 ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ስዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ወይም እለቱ የእረፍት ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን ከቀኑ 8፡30 ስዓት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 13 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ማሳሰቢያ፡- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ

በሰልክ ቁጥር፡- 0583202985/0986813855 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ባህር ዳር ከተማ ፋክስ 058 226 49 62

 

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ

 

Save Tender