Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethio Wetlands and Natural Resources Association (EWNRA)(ኢትዮ ዌትላንድስ ኤንድ ናቹራል ሪሶርስስ አሶሴሽን)
  • Address Jomo Kenyata Street,Bambis,Mekane Yesus blg,Addis Ababa,Ethiopia, Phone: +251115527791
  • Websitehttps://ewnra.et
  • Deadline25 Oct 2024, 2:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Wood And Wood Working

ኢትዮ ዌትላንድስና ናቹራል ሪሶርስ አሶሴሽን (EWNRA) ሀገር በቀል የልማት ድርጅት ሲሆን፣ ማህበረሰብ ተኮር ለሆነ የጋጣ ንብ ማንባት ሥራ አገልግሎት የሚዉል በቁጥር 2,450 (ሁለት ሺ አራት መቶ ሀምሳ) ኬንያ ቶፕ ባር ሞዴል የንብ ቀፎ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::

Ethio Wetlands and Natural Resources Association (EWNRA)(ኢትዮ ዌትላንድስ ኤንድ ናቹራል ሪሶርስስ አሶሴሽን)


የንብ ቀፎ ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮ ዌትላንድስና ናቹራል ሪሶርስ አሶሴሽን (EWNRA) ሀገር በቀል የልማት ድርጅት ሲሆን፣ ማህበረሰብ ተኮር ለሆነ የጋጣ ንብ ማንባት ሥራ አገልግሎት የሚዉል በቁጥር 2,450 (ሁለት ሺ አራት መቶ ሀምሳ) ኬንያ ቶፕ ባር ሞዴል የንብ ቀፎ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::

ስለዚህ በእንጨትና ብረታ ብረት ሥራ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አካላት የጨረታዉን ሰነድ ከጥቅምት 06 እስከ 15፣ 2017 ዓ.ም ባሉት አስር ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኘው ኢትዮ ዌትላንድስና ናቹራል ሪሶርስ አሶሴሽን (EWNRA) ዋና መስሪያ ቤት፣ ኢሉአባቦር ዞን መቱ ከተማ ከሚገኘው ድርጅታችን ጽ/ቤት ወይም ቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን ከተማ ከሚገኘው ድርጅታችን ጽ/ቤት በመቅረብ በብር 100 (አንድ መቶ) በመግዛት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ተወዳዳሪዎች የጨረታዉን ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ ማስገቢያ ታስቦ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኘው ኢትዮ ዌትላንድስና ናቹራል ሪሶርስ አሶሴሽን (EWNRA) ዋና መስሪያ ቤት እንዲያስገቡ እያሳሰብን፣ ጨረታው የሚዘጋው ጥቅምት 15፣ 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሲሆን የጨረታዉ ሳጥን ከቀኑ 8፡30-9፡00 ሰዓት ድረስ ታሽጎ ይቆያል:: ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በተመሳሳይ እለት ማለትም ጥቅምት 15፣ 2017 ዓ.ም በእለተ አርብ ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኘው ኢትዮ ዌትላንድስና ናቹራል ሪሶርስ አሶሴሽን (EWNRA) ዋና መስሪያ ቤት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን::

በጨረታዉ ለመወዳደር መሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች (ቅድመ ሁኔታዎች)

  • በእንጨትና ብረታብረት ሥራ ለ 2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የሙያ ፈቃድ ያለዉ
  • የዘመኑን ግብር የከፈለ
  • በንብ ቀፎ ስራ ህጋዊ እውቅና ካለው ገጠር ቴክኖሎጂ ማሰልጠኛ የሰለጠነና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል::
  • ካሁን በፊት ለሰራባቸዉ ተመሳሳይ ሥራዎች ማለትም ኬንያ ቶፕ ባር ሞዴል ባለፍሬም የንብ ቀፎ ስራ     ከ 3 በላይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል::
  • የሚቀርበው የንብ ቀፎ ሥራ ዋጋ ኢሉአባቦር ዞን መቱ ከተማ ከሚገኘው ድርጅታችን ጽ/ቤት ድረስ የማጓጓዝ ዋጋን ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ
  • የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታ ከገባበት ጠቅላላ ዋጋ መጠን 10% የሚሆን ሲፒኦ (CPO) በባንክ ማስያዝ የሚችል
  • በድርጅቱ አቅራቢነት የሚገባውን የውል ስምምነት ህጎች የሚያከብር፤ ስራውን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ውል ከተገባበት ቀን ጀምሮ ሁለት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሰርቶ የሚያስረክብ
  • ጨረታውን አልፎ ወደ ውል ስምምነት የሚገባ ተጫራች ለቅድመ ክፍያ ዋስትና (Advance guarantee) የሚሆን ለሁለት ወራት ጸንቶ የሚቆይ ውል ከገባበት መጠን 30% የሚሆን የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ወይም ሲፒኦ (CPO) ድርጅቱ በሚያስቀምጥለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ማቅረብ/ማስያዝ የሚችል

ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኘው ኢትዮ ዌትላንድስና ናቹራል ሪሶርስ አሶሴሽን (EWNRA) ዋና መስሪያ ቤት፣ ኢሉአባቦር ዞን መቱ ከተማ ከሚገኘው ድርጅታችን ጽ/ቤት ወይም ቤንች ሽኮ ዞን ሚዛን ከተማ ከሚገኘው ድርጅታችን ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-5527791/047-1411057/ 047-3350634 ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::

ማሳሰቢያ

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ።

 

 

Save Tender