ደደቢት ብድርና ቁጠባ ተቋም አ/ማ የ 2016 ዓ/ም በጀት ዓመት የድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ ወይም የሒሳብ ሥራ በውጭ ኦዲተሮች በጨረታ አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል::
ደደቢት የብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ
በድጋሚ የወጣ የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
ደደቢት ብድርና ቁጠባ ተቋም አ/ማ የ 2016 ዓ/ም በጀት ዓመት የድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ ወይም የሒሳብ ሥራ በውጭ ኦዲተሮች በጨረታ አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል:: የሚከተለው መስፈርት የምታሟሉ የኦዲት ተቋማት /Audit Firms/ እንድትወዳደሩ ድርጅታችን ይጋብዛል::
- ተጫራች በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መስፈርት መሰረት ከAABE (Accounting and Auditing Board of Ethiopia) ፍቃድ ያለው ሆኖ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና ቫት ተመዝጋቢ መሆነ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል::
- ተጫራች የ2016 ዓ/ም የሚገባውን የመንግስት ግብር የከፈለና የ2016 ዓ/ም ንግድ ፍቃድ ያሳደሰ መሆን አለበት::
- ተጫራች ለጨረታው ማስከበርያ የሚሆን ከጠቅላላ ዋጋ ከ2% ያላነሰ በባንክ የተረጋገጠ በCPO ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል::
- ተጫራቹ ለኦዲት ሥራ በዝርዝር ከቀረቡለት ንኡስ ቅርጫፎች፣ ቅርጫፎችና ዋና መስሪያ ቤቱ ጨምሮ በአሰራሩ መሰረት ቢያንስ 50% /አምሳ በመቶ/ ኦዲት የሚደረጉ ሆነው በ2015 ዓ/ም በውጭ ኦዲተሮች ኦዲት ያልተደረጉ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ይሆናሉ::
- ከታች በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሰረት ብቁ የሰው ሃይል በማዘጋጀት ለሥራ የሚሆኑ ሁለት ተሽከርካሪዎች ከድርጅታችን ተመድቦለት ሥራው ከተጀመረ በበኋላ በአንድ ወር ተኩል ወይም 45 ተከታታይ ቀናት ሥራውን ጨርሶ ለድርጅቱ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት::
- ተወዳዳሪው በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመርያዎች መሰረት በማድረግ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት በድርጅታችን ውስጥ በኦዲት ሥራ ያልተሳተፈ መሆን አለበት::
- የኦዲት ሥራ አስኪያጅ /Audit Manager/ በፋይናንስ ተቋማት በኦዲት ሥራዎች ሶስት ዓመትና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ ያለው ሆኖ ሁሉም የኦዲት አባላት ሰፊና ውስብስብ ሥራ ባላቸው የባንኮችና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት የሒሳብ ሥራዎች ኦዲት በማድረግ በቂ እውቀትና ልምድ ያላቸው መሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
- በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ህግ መሰረት ሁሉም የኦዲት ቡድን አባላት የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርቲንግ ስታንዳርድ /IFRS/ መሰረት በማድረግ የሰለጠኑበት ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ ከዚህ በተጨማሪ በIFRS ሥራዎች በቂ እውቀትና ልምድ ያላቸው መሆን ይገባቸዋል::
- ተጫራች አሁን ባለው ሁኔታ በጥሩ አቋም የሚገኝ፣ በህግ ያልታገደ ወይም ያልተከሰሰ፣ የመፍረስ አደጋ ያልተጋረጠበት መሆን አለበት::
- በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መለክያዎች የኦዲት ቡድን አባላት በንብረት ዋጋ አወሳሰንና አተማመን በተመለከተ በቂ ስልጠና የወሰዱ እንዲሁም በእውቀት የተመሰረተ ትክክለኛና ፍትሃዊ ግምት ማስቀመጥ የሚችሉ፣ ሰፊና ውስብስብ የማይክሮ ፋይናንስ ሥራዎችና የሚጠቀምባቸው አሰራሮች የመገምገምና የመረዳት ችሎታ ያላቸው መሆን ይገባቸዋል::
- በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የኦዲት ኣሰራር መሰረት በማድረግ የኦዲት ቡድን አባላት የኦዲት ሥራው በትክክለኛ መንፈስና ነፃነት ሥራቸው ለማከናወን ሲባል ባለፉት ሶስት ዓመታት የማይክሮ ፋይናንሱ ሰራተኛ ያልነበሩ መሆናቸው ማረጋገጥ ይገባል::
- በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የስነ ምግባር መስፈርቶች መሰረት በማድረግ የሚከተሉት አካላት የውጭ ኦዲት አጋር ወይም አባላት አለመሆናቸው በሚቀርብለት ቃለ-ማሃላ ማረጋገጥ የሚችል::
- ኦዲት ለሚደረገው ተቋም ባለ አክስዮን /Shareholder/ ዳይሬክተር ወይም የማይክሮ ፋይናንስ ሰራተኛ አለመሆናቸው፣
- በፍርድ ቤት ያልተገባ ሥራ በመሥራት ኪስራ የታወጀበት አለመሆኑ፤
- በማንኛውም ወንጀል ወይም የወንጀል ድርጊት ማለት በማጭበርበር ወይም በማታለል፤ በገንዘብ ወንጀል ወይም በሌሎች ህገወጥ ተግባራት በመሳተፍ በፍርድ ቤት ያልተፈረደባቸው መሆናቸው፤
- በማንኛውም የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ወይም በሌላ የገንዘብ ተቋም አባል አለመሆናቸው፣
- በማንኛውም የግብር ግዴታ ተጠያቂ አለመሆናቸው ማረጋገጥ የሚችል::
- በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የውጭ ኦዲተሮች መርህ መሰረት የውጭ ኦዲተር፣ የሥራ አጋሮቹ ወይም የሒሳብ ቡድን አባላት እንዲሁም ተባባሪዎቻቸው ምንም ዓይነት የተቀማጭ ሒሳብ እንዳይሰሩና በክንድ ርዝመት ካልሆነ በስተቀር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተበዳሪ ወይም የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ተጠቃሚ አለመሆናቸው ማረጋገጥ ይገባዋል::
- በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መስፈርቶች መሰረት በኦዲት ውል ላይ አንድ የኦዲት ድርጅቱ በባለቤትነት፣ በዳይሬክቶሮችና በሥራ አስኪያጆች ላይ በሚኖረው ለውጥ ምክንያት በዚህ መመርያ ላይ የተቀመጠውን መስፈርት ሳይፈፅም ከቀረ እንዲሁም በድርጅቱ ወይም በማናቸውም የሒሳብ ቡድኑ አባላት ላይ የሚወሰድ ማናቸውም ዲስፕሊን ወይም ህጋዊ እርምጃ ውሉ ሊሰረዝ እንደሚችል በግልፅ መታወቅ አለበት::
- በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመርያ በሚያዝዘው መሰረት አንድ የውጭ ኦዲተር ለእያንዳንዱ ቀጠሮ ወይም ዳግም ቀጠሮ በዚህ መመርያ Annex I እና II መሰረት ቀደም ተከተል የፃፈውን የነፃነት ማረጋገጫ እና ተገቢ አዋጅና ፎርም አክብረው ጨርሰው እንዲያቀርቡ ያስፈልጋል::
- ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ከጥቅምት 04/02/2017 ዓም ጀምሮ ከደደቢት ብድርና ቁጠባ ተቋም ዋና መስሪያቤት መቐለ ቅርጫፍ ቁጥር 2 ከሚገኘው ፅ/ቤታችንና አዲስ አበባ ላይዘን ኦፊስ ቦሌ ዳሞ ሆቴል አከባቢ ከሚገኘው ፅ/ቤታችን ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል መውሰድ ይቻላል::
- የጨረታ ሳጥን ክፍት ሆኖ የሚቆየው ከጥቅምት 04/02/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 13/02/2017 ዓ/ም ከጥዋቱ 4፡00 ሆኖ የጨረታ ሳጥን በዚህ ቀን ልክ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደደቢት ብድርና ቁጠባ ተቋም አ/ማ በ4ኛው ፎቅ የፋይናንስ ክፍልና በአዲስ በአዲስ አበባ ላይዘን ኦፊስ ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ህጋዊነቱ እስከ ጠበቀ ድረስ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል::
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለፀ በኋላ በተከተታይ 7 ቀናት ውስጥ ወደ ድርጅቱ የንብረትና ግዢ አስተዳደር ቀርቦ ውል ማሰር አለበት::
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከታወቀ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋ 10% un conditional bank guarantee ማስያዝ አለበት::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ መቐለ ዋና ቢሮ ሞባይል ቁጥር +251963095665
አዲስ አበባ ላይዘን ኦፊስ +251928277756 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
ደደቢት የብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ
መቐለ
