የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 1 ጠቅላላ ስራ ወይም የመንገድ ስራ ተቋራጭ GC-/RC-1 የሆኑ የአገር ውስጥ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ የወላይታ ሶዶ አየር ማረፊያ ዲዛይን ክለሳ እና ግንባታ ፕሮጀክት (Design Review and Build of Wolayta Soddo Air- field project ) ለማሰራት ይፈልጋል::
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ -SSNT-T497
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 1 ጠቅላላ ስራ ወይም የመንገድ ስራ ተቋራጭ GC-/RC-1 የሆኑ የአገር ውስጥ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ የወላይታ ሶዶ አየር ማረፊያ ዲዛይን ክለሳ እና ግንባታ ፕሮጀክት (Design Review and Build of Wolayta Soddo Air- field project ) ለማሰራት ይፈልጋል:: የፕሮጀክቱ የማጠናቀቂያ ጊዜ 730 የካላንደር ቀናት ይሆናል:: ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል:: ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 04 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ለመውሰድ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በሂሳብ ቁጥር 1000006958277 (E- 99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ጨረታ ቁጥር (SSNT-T497) በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል:: ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን በኢሜል ያገኛሉ።
የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 / አምስት መቶ ሺህ/ ብር በባንከ የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት
የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል:: ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የቴከኒካል እና የፋይናንሺያል የመጫረቻ ሠነዳቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ ህዳር 04 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 09:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው:: ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት ግቢ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ህዳር 04 ቀን 2017 በ 09:5 ሰዓት ይከፈታል::
ለተጨማሪ ማብራሪያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ወ/ሮ ሰላማዊት አባተ
ስልክ ቁጥር፡ 011-517-42-58
ኢ-ሜይል፡ selamawia@ethiopianairlines.com
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከሁለት በላይ ፕሮጀክት በማከናወን ላይ የሚገኙ እና የግንባታቸው አፈፃፀም ከ70% በታች የሆነ ተጫራች ጨረታው ላይ መሳተፍ አይችሉም::
ጨረታው በይፋ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ላሉት 15 ተከታታይ ቀናት የጸና ይሆናል።
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
