Tender Detail

Tender Details

  • Company Sabata Polytechnic College (ሰበታ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
  • Address , Phone: 0113383843
  • Website
  • Deadline04 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Educational And Training Equipment And Machinery

የሰበታ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ 2017 በጀት ዓመት ለሥልጠና አገልግሎት የሚውሉ፤ የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Sabata Polytechnic College (ሰበታ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)


ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ሰበታ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ 2017 በጀት ዓመት ለሥልጠና አገልግሎት የሚውሉ፤

1. የኮንስትራከሽን ዕቃዎች

2. የኤሌክትሪክ እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

3. ለአውቶሞቲቭ ስልጠና የሚውሉ ዕቃዎች

4. ለብረታ ብረት ሥልጠና የሚያገለ ግሉ ዕቃዎች

5. ለልብስ ስፌት እና ቴክስታይል ማሠልጠኛ ዕቃዎች

6. ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማሰልጠኛ ዕቃዎች

7. ለሥልጠና የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዕቃዎች እና

8. የቢሮ ፈርኒቸሮችን እንዲሁም

9. የእንስሳት መኖ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን ግብር አጠናቀው  ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ (Clearance) ማቅረብ የሚችሉ፤ አቅራቢዎች ዕቃውን ለማቅረብ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ፡፡
  2. ተጫራቾች ዝርዘር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ከኮሌጁ ፋይናንስ ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት ለአንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰበታ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሂሳብ ቁጥር 1000016069225 በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ በተዘጋጀው ሰነድ የቀረበውን ዋጋ (1%) በባንከ በተመሰከረለት CPO በሰበታ ፖሊ ቴከኒክ ኮሌጅ ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚሸጡበትን ዋጋ በመጥቀስ በፖስታ በማሸግ በተባለው ቀን ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ ሞልተው የሚያቀርቡትን ዋናና ፎቶ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ስምና አድራሻ በማድረግ በድርጅቱ ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫትን (15%) ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች ያሸነፏቸውን ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ያሸነፏቸው ዕቃዎች ገቢ የሚሆኑት አስፈላጊውን ጥራት ማሟላታቸው በባለሙያ ሲረጋገጥ ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ከስቶከ መሆን ይኖርበታል፡፡
  10. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሁሉም የጨረታ ማስታወቂያ በ22ኛው ቀን  ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን 4:30 የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. ከላይ የተገለጸው የመከፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

    ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር- 0113383843/0113380022

 

ሰበታ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Save Tender