ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለተለያዩ አግልግሎት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሸከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር መሸጥ ይፈልጋል፡፡
MIDROC INVESTMENT GROUP (ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ)
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር -Disposal 0002/2017
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለተለያዩ አግልግሎት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሸከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ
በማወዳደር መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
- በጨረታ የሚሳተፍ ድርጅት የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች አዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ በሸገር ዱቄትና ፋብሪካ ቢሮ ቁጥር 04 በአካል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በፋርማ ኪውር ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም በዳሸን ባንከ የሂሳብ ቁጥር 0307202694011 በማስገባት ያስገበበትን ደረሰኝ በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራች በጨረታው ለሚሳተፍባቸው ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ለጨረታ ያቀረቡትን 10% የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚፈልጓቸውን የተሽከርካሪ ዓይነትና የሠሌዳ ቁጥር ድርጅቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስ እንዲሁም ከሲፒኦ ጋር በማካተት የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እስከ አስራ ሶስተኛው ቀን 4፡30 ድረስ ሸገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቢሮ ቁጥር 04 ለመረጡት ተሽከርካሪ ፋይናንሺያል ፕሮፖዛላቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማዘጋጀት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ፤ ጨረታው በዕለቱ 4፡45 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች አዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ በሸገር ዱቄትና ፋብሪካ ቢሮ ቁጥር 04 ቅጥር ግቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት አስራ ሶስት የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ተሽከርካሪዎቹን ማየት ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ ማንኛውንም የመንግስት ዕዳ ከፍሎ ተሽከርካሪዎቹን ለመሸጥ የሚያስፈልግ ክሊራንስ በራሱ ወጪ ከሚመለከተው የመንግሥት መ/ቤት ያቀርባል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዎች ለሚገዟቸው ተሸከርካሪዎች የስም ማዛወሪያ ወጪ በራሳቸው ይሸፍናሉ፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ /ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለጸለት በ6 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን ተሸከርካሪ ሙሉ ዋጋ ገቢ በማድረግ ተሽከርካሪውን ማንሳት ሲኖርበት ተሽከርካሪውን ማንሳት ካልቻለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው CPO እንዲወረስ ይደረጋል፡፡
- በጨረታው የተሸነፈ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ CPO ለተጫራች እንዲመልስ ይደረጋል፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ ህጋዊ መብት አለው፡፡
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሸገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቢሮ ቁጥር 04
ማሳሰቢያ፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251913953038/+251912192662/+251911663804 ይጠቀሙ።
- ተጫራቾች ሙሉ አድራሻ እና አማራጭ ስልኮቻቸውን መጥቀስ ይኖርባቸዋል፡፡
ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
