Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ፅ/ቤት
  • Address በሀዋሳ ከተማ ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አጠገብ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-220-42-24
  • Website
  • Deadline27 Oct 2024, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cargo Vehicle

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት ለሠራተኞች ሰርቪስ እና የመስክ መኪና አገልግሎት የሚውል መኪናዎች መከራየት ይፈልጋል ።

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ፅ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት ለሠራተኞች ሰርቪስ እና የመስክ መኪና አገልግሎት የሚውል መኪናዎች መከራየት ይፈልጋል ።

ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እንዲሁም የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈለ ሆኖ እነኝህን ማስረጃዎች አደራጅተው ማቅረብ የሚችሉ እና በግዥ ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

  • ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና የተጫራቾች መመሪያ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) አንደኛ ፎቅ የግዥ፤ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 210 በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት 2% በC.P.O ያስያዙበትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ ዋናውንና አንድ ኮፒ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ፓስታ በማድረግ አንደኛ ፎቅ የግዥ፤ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
  • የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት አንደኛ ፎቅ የግዥ፤ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል።
  • የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል።
  • ቢሮው ለዚህ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ ፡- በስልክ ቁጥር 046-220-42-24 ይጠቀሙ።

አድራሻ፡- አሮጌ ገበያ አለ በጅምላ ጎን

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ፅ/ቤት

Save Tender