በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ለሰራተኞች አገልግሎት የሚውል የታሸገ ½ ሊትር ውሃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2017 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ለሰራተኞች አገልግሎት የሚውል የታሸገ ½ ሊትር ውሃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች, አቅራቢዎች/ ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶችና ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የቲን ሰርተፍኬት፣ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያገለግል ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት አምራች ድርጅቶች እና አምራች ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለታሸገ ውሃ የሞሉትን ዋጋ 25 በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 100 /መቶ ብር /ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በአፄ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ ወደ ዲያስፖራ በሚወስደው አስፓልት መንገድ የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽ ድርጅት ጎን በሚገኘው የጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 304 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በጥንቃቄ በመሙላት በሚገባ በኤንቨሎፕ ፖስታ በማሸግ እና ዋጋ መሙያው ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በግልጽ በማስቀመጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ 3ኛ ፎቅ የግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 306 ከጠዋቱ 4:30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን የህዝብ በዓል ወይም እሁድ ከሆነ በ17ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ተዘግቶ 4:30 ሰዓት ይከፈታል ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የንግድ ማስረጃዎች ኦርጅናል ለብቻ አቅርበው ማሳየት ይኖርባቸዋል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር :- 0583207051/0583206641/0582263346/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት
