Tender Detail

Tender Details

  • Deadline02 Nov 2024, 3:48 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Construction Machinery

ድርጅታችን ሱር ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማሕበር በተለያዩ ፕሮጀክቶች ሊሰሩ የሚችሉ የተለያዩ የኮንስትራከሽን ማሽነሪዎች እና ተሽከርካሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት (መከራየት) ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሱር ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማሕበር በተለያዩ ፕሮጀክቶች ሊሰሩ የሚችሉ የተለያዩ የኮንስትራከሽን ማሽነሪዎች እና ተሽከርካሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት (መከራየት) ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ላይ መወዳደር የምትፈልጉ ደምበኞች (ተጫራቾች) በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ልታሟሏቸው የሚገባችሁ ዝርዝር ሁኔታዎች ፡-

1. የማሽኑ ወይም የተሽከርካሪው የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር (ሊብሬ)

2. ተጫራቾች የ 2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርቲፊኬት፣ እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ፤

3. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀ ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ከ 23/01/2017 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) እየከፈሉ በአዲስ አበባ ቦሌ ሜጋ ህንፃ አጠገብ ከሚገኘው ዋና መስሪያቤታችን፤ በመቀሌ ላጪ ከሚገኘው ቅርንጫፍ መስሪያ ቤታችን መውሰድ ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች ከድርጅታችን የተሰጣቸው ኦርጅናል ፎርም ብቻ ተጠቅመው ያለ ስርዝ ድልዝ ቫት ሳይጨምር (ከቫት በፊት) ለእያንዳንዱ አይነት ማሽን ወይ ተሽከርካሪ በጥንቃቄ ነጠላ ዋጋ ሞልተው፤ ፈርመው እና ማህተም አድርገው በታሸገ ኤንቨሎፕ እንዲልኩልን ወይም ጨረታው በሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት በአካል ይዘው መምጣት አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበርያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ) ሲፒኦ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡

6. ለድርጅታችን ስራ የሚውል የነዳጅ ወጪው በድርጅታችን የሚሸፈን ይሆናል፡፡

7. የማጓጓዣ ወጪን (ዋጋ) በሚመለከት ወደ ፕሮጀከት ለማጓጓዝ የሚያስፈልግ ወጪ በድርጅታችን የሚሸፈን ሲሆን ከፕሮጀከት ለማውጣት (ለመመለስ) የሚያስፈልግ ወጪ በአከራይ (በደምበኛ) የሚሽፈን ይሆናል፡፡

8. አንድ ተጫራች (ደምበኛ) ከተጠቀሱት አይነት ማሽኖች እና ተሽከርካሪዎች በፈለገው አይነት ማሽን/ተሽከርካሪ ብቻ የመጫረት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

9. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 25/02/2017 ዓ.ም ሰኞ ከጠዋቱ 4:00 (አራት ሰአት) አዲስ አባባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1601 እንዲሁም በመቀሌ ላጪ በሚገኝ ቅርንጫፍ መስሪያቤታችን ሁኖ ጨረታው ሲከፈት የተገኘም ሆነ ያልተገኘ ደምበኛ በውጤቱ ተገዢ ይሆናል፡፡

10. ጨረታውን ያሸነፈው ተወዳዳሪ/ተጫራች ያሸነፈው ብዛት እና ዓይነት ማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ሊያቀርብ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በአምስት ተከታታይ ቀን ውስጥ ላሸነፈበት ዓይነት እና ብዛት ማሽነሪ እና ተሽከርካሪ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ጨረታውን ያሸነፈው ደምበኛ ተጫራች ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በአምስት ተከታታይ ቀን የሚፈለገው አይነት እና ብዛት ማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ማቅረብ ካልቻለ፤ እሱ ባሸነፈበት ዋጋ ሌሎች ደምበኞች አቅራቢዎች ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡

11. ድርጅታችን የተሻለ ኣማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር 0991190434/0914297662 ወይ በአካል መጠየቅ ይችላሉ

ሱር ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማሕበር

Save Tender