Tender Detail

Tender Details

  • Company የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (FDRE Refugees and Returnees Service)
  • Address የእንቁላል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ ከፌዴራል ፖሊስ ክበብ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 813 21 93
  • Websitehttps://rrs.et/
  • Deadline17 Oct 2024, 12:24 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Textile, Garment & Leather

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የሰራተኞች የደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (FDRE Refugees and Returnees Service)


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የሰራተኞች የደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ተጫራቾች -

 

  1. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ክሊራንስ፣ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ እና በጨረታ ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው::

 

  1. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ወይም ሂሣብ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ቅዳሜና እሁድ የመስሪያ ቤቱ የስራ ቀናት አይደሉም፡፡

 

  1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዳቸውን በአገልግሎት ዋና መ/ቤቱ የግዢ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡

 

  1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት Refugees and Returnees Service በሚል የተዘጋጀ የባንክ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም የባንከ ዋስትና (Bank Guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

 

  1. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 04፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

 

  1. አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

ኣድራሻ፣ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት

ምስኪ ህንፃ

ከዋሸንግተን የህከምና ማዕከል 500 ሜትር እንደተጓዙ

ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ከታክሲ ተራው በቀኝ በኩል

ለተጨማሪ ማብራሪያ፤

በስልክ ቁጥር 011 813 21 93 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት

አዲስ አበባ

Save Tender