የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር EEU/PMO/NCB/08/2016
የኢትዮጺያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፓርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት የከባድ ተሽከርካሪ ጎማዎችን በዘረፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ የተመለከቱት መስፈርቶችን የሚያJሉ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው የታደስ የንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ በኢ ፌዲሪ የመንግሰት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገጽ በአቅራቢዊች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው
- የጨረታ ሰንዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የኢ ኤ እ ፕሮጅክት ፓርትፎሊዮ ማኒጀመንት ጽ/ቤት ማህበራዊ ዋስትና ህንጻ ላይ 11ኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,00(ሁለት መቶ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኃላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለውን የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በኢ ኤ አ ፕሮጀክት ፓርትፕልዮ ማኔጅመንት ወይም EEU-PMO ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰንዱ ጋር ማቅረብ ኣለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EEU/PMO/NCB/08/2016 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ የካቲት 2 ቀን 2016 ዓ/ም እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በኢ ኤ አ ፕሮጀክት ፓርትፎዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ማህበራዊ ዋስትና ህንጻ ላይ 11ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣\
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም/ የካቲት 2 ቀን 2016 ዓ/ም እስከ ቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2:00-6:00 እና ከሰዓት በኃላ ከ7፡00 11:00 መመልከት ይቻላል።
- የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 01112631559 መደወል ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
የፕሮጀክት ፓርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት
