ጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ት/ጽ/ቤት የተተወና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ የሀዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ት/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተውና ተወርሰው የሚገኙ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የማስዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች የተሽከሪካሪ መለዋወጫዎች እና ደረቅ ጫት ባሉበት ሁኔታ በግልፅና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች ማJላት ይኖርባቸዋል።
- የግልፅ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች በዘርፉ ተታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል። ግምታዊ ዋጋው ከብር 500ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
- የደረቅ ጫት ተጫራቾች በዘርፉ የላኪነት ፈቃድ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/ በመክፈል በት/ጽ/ቤቱ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን C.P.O የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
- ለደረቅ ጫት ሐራጅ ጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለኮዱ 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር) በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO ማቅረብ ይኖርበታል።
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የንብረቶቹን ናሙና በመደበኛ የሥራ ሰዓት በሀዋስ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡05 ሰዓት አዲስ መጋዘን ይካሄዳል። የሐራጅ ጨረታው የግልጽ ጨረታው ከተጠናቀቀ ከ10 ደቂቃ በኃላ ይካሄዳል። ነገር ግን ጨረታው በበዓል/ዕሁድ/ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት የሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይሆናል።
- ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦት ከነቫት በሚለው መስመር በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸግ ኤንቨሎፕ ወይም ፓስታ ማቅረብ አለባቸው። ከዚህ ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ለመቀበል አይገደድም።
- ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በጨረታ ሰነድ ላይ የተሰጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥ እና ማሻሻል አይችልም።
- ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድርስ ፀንቶ ይቆያል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታ ከተከፈት በኃላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም።
- በጨረታው ለተሽነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በሶስት የሥራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ከሽያጭ ጋር የሚታሰብላት ይሆናል።
- ተጫራቾች ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡና ችግር ቢፈጥር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
- ለጨረታው የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው ።
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሽነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተግለፀበት ቀን ጀምሮ በ5(አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደረጉ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ በጨረታ ላይ ይወጣል።
- ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታ ላይ ይወጣል።
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፦ 0462125396
ጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
