Tender Detail

Tender Details

  • Deadline15 Jan 2024, 11:09 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Construction Machinery

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አ.ገ.መ.ኮ.ኤ 08/2016


የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለዋናው መ/ቤት መቆጣጠሪያ ቦንድ /በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያJሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።

  1. የዘመኑ የታደስ ሕጋዊ የፀና የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
  3. 200,000.00(ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰንዱ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ፟-ሰዓት በመምጣ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጄንሲ ዋናው ቢሮ ባህርዳር ከተማ ከሚገኘው ከገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰንዱን ቴክኒካልና ፋይናንሻል በመለየት በተለያየ ፓስታ በጥንቃቄ በማሽግ ከኤንጀንሲው መ/ቤቱ ግዥ ኦፊሰር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከተጋበዙበት ከ 30/04/2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 15/05/2016 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ ፒ ኦ ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በማያያዝ  በታሽገ ፓስታ አድረገው ማቅረብ አለባቸው።
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሂሳቡን በአንድ ቅጅ በጥንቃቄ በታሽገ ፓስታ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ከ30/4/2016 ዓ/ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ጥር 15 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ግንባታ ግባዓት አቅርቦት ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 ጥር 15 ቀን 2016 ዓ/ም በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል።
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲ መ/ቤት ግዥ አፊሰር ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 0583205155/058221107 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 0582221100 በመላክ ማግኘት ይቻላል።

አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ፓ.ሣ ቁ 382 ባህር ዳር

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገጠር መንገዶች

ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

Save Tender