የማሽን ኪራይ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአንጎለላና ጠራ ወረዳ የጨኪ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በከተማው የውስጥ መንገድ ጠረጋና ጠጠር ማልበስ ስራ ለመንገድ ስራ አገልገሎት የሚውል 330 ካት (CAT) ኤክስካቫተር በአካፋ እና ከነጃክ ሀመሩን ጨምሮ 2015 ሞዴል እና ከዚያ በላይ የሆነ ለ85 ሰዓት፤ ግሬደር 140 hp 2015 ሞዴል እና ከዚያ በላይ የሆነ ለ100 ሰዓት ሮሎ 16 ቶን እና በላይ ክብድት ያለው 2015 ሞዴል እና ከዚያ በላይ የሆነ ለ35 ሰዓት የውሃ ቦቲ ከ10 ሺህ ሊትር በላይ የመያዝ አቅም ያለው ዘመናዊ ውሃ መርጫ ያለው ለ5 ቀን እና ሲኖትራክ 16 ሜትር ኩብ እና በላይ የሚጭን ሆኖ የስሪት ዘመኑ 2015 ሞዴለ እና ከዚያ በላይ የሆነ 300 ቢያጆ ሆኖ ለሁሉም ስራዎች ማሸን ከነዳጅና ሰርቪስ አገልግሎት ጭምሮ ተከራይቶ ማሠራት ይፈልጋል።
ስለሆነም፦ በጨረታው ለመካፈል የምትፈልጉ፦
- 140 HP ግሬደር የስሪት ዘመኑ 2015 ሞዴል እና ከዚያ በላይ ሆኖ ለ100 ሰዓት የሚሰራ ፤ ማሽኑ ሊወጣና ሲገባ የሚያስፈልገውን መጎጎዣ /ሎቤድ/፣ ኦፕሬተር በስራ ወቅት የሰርቪስ፣ የነዳጅ እና ቅባት አቅርቦት ራሱን ችሎ የሚሰራ ወይም ሙሉ ለሙሉ ወጭውን መሸፈን አለበት።
- 330 HP ካት (CAT) ኤክስካቫተር በአካፋ እና በጃክሀመር መስራት የሚችል የስሪት ዘመኑ 2015 ሞዴል እና ከዚያ በላይ የሆነ ለ85 ሰዓት፤ የቆረጣ ስራው የሚከወናነው በጨኪ ንዑስ ከተማ ቀጠና 04 በከተማ ውስጥ ወደ አዲስ አበባ ከሚያልፈው ዋና መንገድ ጀምሮ እስከ አዲሱ ገበያ እና ፒያሳ የመኖሪያ ቤት ስራ እና አካባቢ ልማት ማህበር ጀርባ የተሰጠ የቤት መስሪያ ቦት መካከል ሲሆን ለመንገዱ ሙሌት የሚሆነው ማቴሪያል የሚመረትበት አካባቢ ደግሞ በከተማው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ከሚሰራበት በጨኪ ንኡስ ከተማ የሚገኘው መርቆሪዮስ ቤተክርስቲያን ጀርባ ውስጥ ገባ ብሎ በተመረጠ ማቴሪያል ያለበት ቦታ ድረስ ላይ የሚሰራ ማሽኑ ሲወጣና ሲገባ የሚያስፈልገውን መጎጎዣ /ሎቤድ/ ኦፕሬተር በስራ ወቅት የሰርቪስ የነዳጅ እና ቅባት አቅርቦትን አካቶ ወይም ራሱን ችሎ መስራት አለበት።
- ሮሎ 16 ቶን እና በላይ ክብደት ያለው የስሪይ ዘመኑ 2015 ሞዴል እና ከዚያ በላይ የሆነ ለ35 ሰዓት፤ የሚሰራ ማሸኑ ሲወጣና ሲገባ የሚያስፈልገውን መጎጎዣ /ሎቤድ/ ፣ ኦፕሬተር በስራ ወቅት የሰርቪስ የነዳጅ እና የቅባት አቅርቦት አካቶ ራሱን ችሎ የሚሰራ መሆን አለበጥ
- ሲኖትራክ 16 ሜትር ከብ እና በላይ የሚጭን ሆኖ የስሪት ዘመኑ 2015 ሞዴል እና ከዚያ በላይ የሆነ 300 ቢያጆ በከተማው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ላይ ጭኖ ማቅረብ የሚችል መኪናው ሲንቀሳቀስ የሚያስፈልገውን ሹፌር በስራ ወቅት የሰርቪስ ያነዳጅና ቅባት አቅርቦትን ራሱን ችሎ የሚሰራ ወይም ሙሉ ለሙሉ ወጭውን መሸፈን አለበጥ
- ዘመናዊ የውሃ ቦቲ ለ5 ቀን፣ 10 ሽህ ሊትር እና ከዚያ በላይ የመያዝ አቅም ያለው የውሃ መርጫዎቹ (ማርከፍከፊያዎቹ ) ዘመናው የሆኑ እና ምቹ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በሞሉት ዋጋ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ማድረኛ በፍሉድ መደለዝ አይፈቀድም፤ ምን አልባት በጠቅላላ ዋጋ ላይ ስህተት ቢፈጥር አንድ ዘርዝ አድርጎ ስለ መሰርዙ ፊርማ ማስቀመጥ አለበት።
- ከላይ የተጠቀሰውን የማሽን ሞዴል ሲያስገባ በሊብሬ ሊረጋገጥ የሚችል መሆን አለበጥ
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ቫትን አካቶ ነው።
- የዘመኑ ግብር፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /tin Number/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ኮፒውን አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የመልካም የስራ አፈጻጸም ማስረጃ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ስራውን በተሰጠው ማስረጃ ዲዛይንና ጊዜ ውስጥ ሰርተው ማጠናቀቅ መቻል አለባቸው።
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኃላ ባሉት በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውለታ መፈጸም አለበት።
- የጨረታ ሰነዱን አንጎለላና ጠራ ወረዳ ጨኪ ንዕስ ማዘጋጃ ቤት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 250 ሁለት መቶ ሀምሳ ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው በመፈረምና የድርጅት ማህተም በማድረግ ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በጨኪ ንኡስ ማዘጋጃ ቤት በመሂ 1 የሚያሲዙ ከሆን ያስያዙበትን ደረሰኝ ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በመለየት ዋና ኮፒ እና 2% የተያዘበትን ማስረጃ በጥንቃቄ በማሸግ እንዲሁም በፖስታው ላይ በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የተከራይ መ/ቤቱን የተጫራቾችን ስምና አድራሻ እንዲሁም የግዥውን አይነት አገልግሎት ግዥ ፈጽጻሚ በመጥቀስ ይህ ማስታወቃያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በእለቱ በ31ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ይታሸግና በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ ይከፈታል።
- 31ኛው ቀን የስራ ቀን ካልዋለ ጨረታው በሚቀጠለው የስራ ቀን ይከፈታል ።
- ማንኛውም አይነት የስራ ልዩነት ካለ ማስተካከያ ያደርግበታል።
- ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ በኃላ ስራውን ሙሉ በሙሉ ለመስራት የተወከሉ ሰዎች ደርጃቸው አቻ እና በላይ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በአንዱ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- ነዳጅ፣ ቅባትና ሰርቪስ አገልግሎት አቅርቦት እና የማሽኑን ነዳጅ የሚሞላውን የጉልበት ሰራተኛ ዋጋ በተጫራቹ ይሸፈናል።
- ማንኛውም ኮፒ የሚደረጉ ማስረጃዎች በትክክል መነበብ እና መታየት አለባቸው።
- በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ማሻሻያ ማድርግ አይቻልም።
- አሸናፊ ተጫራች የሚለየው ቫትን ጨምሮ በሁሉም ማሽኖች የኪራይ ዋጋ ድምር ነው።
- ኤክስካቫተር፣ ግሬደር፣ የውሃ ቦቲ ሮሎ ማሸኑና ሲኖትራክ ሲመጣ በአስፓልት ከአዲስ አበባ 100 ኪ/ሜ ከደብረ ብርሃን አስፓልት 27 ኪ/ሜ ነው።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።ሆኖም ከተጠቀሱት ማሽኖች ውስጥ ከመንግስትም ሆነ ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ድጋፍ የሚያገኝ ከሆን ለመከራየት አይገደድም።
- የጨረታ ሰነዱ የሚሸጠው የግሬደር ኤክስካቫተር ሮሎ ማሽነሪ እና ሲኖትራክ ኪራይ ነዳጅና ቅባት ሰርቪስ አገልግሎት ተካቶበት በአንድ ሰነድ ነው።
- የማሽነሪዎቹ አግባብ ተከራዩ መ/ቤት በሚያወጣበት ቅደመ ተከተል መሰረት ማለትም
ሀ)ኤክስካቫተር፡ ይህ ማሽን ከሁሉም ማሽኖች ቀድሞ መግባት አለበት።
ለ) ግሬደር፦ይህ ማሽን ኤክስካቫተር ማሽኑ በገባ ከ140 እስከ 150 ሰዓት ውስጥ መገባት አለበት።
ሐ) ሮሎ፦ ይህ ማሽን ኤክስካቫተር ማሽኑ በገባ ከ140 እስከ 150 ሰዓት ውስጥ የመግባት ግዴታ አለበት።
መ) ሲኖትራክ (Dump truck):- ሲኖትራኩ ኤክስካቫተር ማሽኑ ሰገባ እኩል መግባት አለበት።
ሰ) የውሃ ቦቲ (shower truck)፦ የውሃ ቦቲው ግሬደር እና ሮሎ ሲገባ እኩል መግባት አለበት።
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ፡011-890-03-01 ደውለው ይጠይቁ።
የጨኪ ንኡስ ማዘጋጃ ቤት
