ግልጽ የጨረታ ማስታወቃያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2016 በጀት አመት ለ2ኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
1ኛ። አላቂ እና ቆሚ የቢሮ እቃዎች (stationary) የጽዳት እቃዎች የደንብ ልብስ፤
2ኛ። የአመት ውል የቢሮ ማሽን ጥገና (ኮምፒተር፤ ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሸን ሰርቪስና ጥገና ጀነሬተር ሰርቪስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሞሉ አቃራቢ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ተጫራቾች የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና የ2016 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- የቫት ተመዝጋና ህጋዊ የአቅራቢነት ማስረጃ ያላቸው መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ክፍል 6 ውስጥ የተገለጽትን እቃዎች ዝርዝር ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ቂ/ክ/ከተማ ወረዳ 4 ፍይናንስ ጽ/ቤት ለዚህ የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ክፍል 6 ውስጥ የተገለጽትን እቃዎች ዝርዝር ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ቂ/ክ/ከተማ ወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለዚህ የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታ ማስከበሪያ ብር ለሁሉም እቃዎች 15,000.00(አስራ አምሰት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና የማስገባት ግዴታ አለባቸው።
- አሸናፊ ድርጅቶች በናሙናው መሰረት ደረጃውን የጠበቀ እቃ የማስገባት ግዴታ አለባቸው።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚያኑ ቀን 4፡30 ሰዓት በፋ/ጽ/ቤት ይከፈታል። 11ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላየ በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
- መቅረብ ያለባቸው መረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ሲሆን ሁለቱም ለየብቻቸው መታሸግ አለባቸው። ነገር ግን ጨረታው ሲከፈት የሚከፈተው ከፒው በመሆኑ ሲፒኦ(CPO) እና ሌሎች አስፈላጊ የሆነ መረጃዎች በሙሉ ኮፒው ውስጥ መደረግ አለባቸው በሁለቱም ኤንቨሎፕ ላይ የድርጅቱ ማህተም መደርግ አለበት።
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ድምር 10% የውል ማስከበሪያ ከውል በፊት ማስያዝ አለባቸው የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ቫትን ያካተተ (ቫትን ተጨምሮበት) መቅረብ አለበት ይህንን ያላደረጉ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ።
- ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄዎች ወይንም መረጃ ማግኘት ለሚፈልጉ ስልክ ቁጥር 011-888-30-69 መጠቀም ይችላሉ።
አድራሻችን ደ/ዘይት መንገድ በቅሎ ቤት ላንቻ ከዲና ፓል ሆቴል ጀርባ
ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
ማሰሳበያ፦መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር
ፋይናንስ ጽ/ቤት
